Song Lyrics

ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ

Tesfaye Chala
Wetimedu Tesebiro Ameletiku
ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (2x) እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (4x) ጠላቴ ሊያጠፋኝ ሲሸምቅ የወደኩ መስሎት በእኔ ሊስቅ ነጋሪት ሲመታ ሲያስመታ እምነቴን ጉልበቴን ሊፈታ ቀና ብዬ ባላይ ኖሮ ዓይኖቸን ወደ አንተ አንስቼ በጠፋሁ ነበር አስካሁን በሰልፉ ብዛት ፈርቼ ደካማን የምትረዳ አምላክ አኔን ደርሰህ እረዳኸኝ መከራዬን አሳለፍከው በኮረብታው ላይ አቆምከኝ አዝ፦ ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (2x) እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (4x) ጠንክሮ ብዙ የፈተነኝ የማይገፋ የመሰለኝ ወደቀ እንደ ቀላል ዕቃ ሰማሁት ድንፋታው ሲያበቃ ቀና ብዬ ስመለከት ከመከራዬ ቀን በላይ ለካስ ጌታ አስቦልኝ ቤቴን በበረከት ሊሞላ ሸሸገኝ ከጉያው ገባሁ ከጥላው ሥር አሳደረኝ እዘምራለሁ ለሥሙ በቤቱ ስለተመቸኝ አዝ፦ ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (2x) እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (4x) ኃይሌ ነው እታመነዋለሁ ክብሬ ነው እደገፈዋለሁ ሞገሴ የማያሳፍረኝ በፀጋው የሚደጋግፈኝ መከታዬ ነው ጋሻዬ ሥሙን በእውነት እጠራዋለሁ ስንቱን ሸለቆ ተራራ ከኢየሱስ ጋር አልፌአለሁ ከጐኔ የሚቆም ዘለዓለም እንዴ እንኳን አላሳፈረኝ በአምላኬ ቀን ወጥቶልኛል እንግዲህ ማን ሊቃወመኝ አዝ፦ ወጥመዱ ተሰብሮ አመለጥኩኝ በአምላኬ ጥላ ውስጥ አደርኩኝ እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖልኛል እንግዲህ ማን ይቃወመኛል (2x) እንግዲህስ ማን ይቃወመኛል (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection