Song Lyrics

ምህረቱ

Tesfaye Chala
Wetimedu Tesebiro Ameletiku
አዝ፦ አቤት (3x) ይሄ ጌታ አቤት (3x) ምህረቱ (2x) አቤት ምህረቱ ምህረቱ እሆሆ (3x) አቤት ቸርነቱ ቸርነቱ አሃሃ (3x) አቤት በጐነቱ በጐነቱ ኦሆሆ (3x) ምህረት በዛ ለምስኪኑ ተስፋ አለው በዘመኑ ተቆጠረ ከሰው ጋራ እርሱ ይናገር እርሱ ያውራ ስንቱ አበሳው ተራግፎለት እንደሰው ዛሬ አምሮበት በአደባባይ ቆሞ ይሄዳል ይሄ ጌታ እንዴት ይገርማል አዝ፦ አቤት (3x) ይሄ ጌታ አቤት (3x) ምህረቱ አቤት ምህረቱ ምህረቱ እሆሆ (3x) አቤት ቸርነቱ ቸርነቱ አሃሃ (3x) አቤት በጐነቱ በጐነቱ ኦሆሆ (3x) የተጣለ ከሰው ደጃፍ መከርን አየ በስንቱ አፍ እዩት ዛሬ ይኸው ቆመ ደረቁ ዛፍ ለመለመ ጥላ ሆነ ለደከሙ ጠላቶቹ ሁሉን ሰሙ ድንቅ ተባለ በምስኪን ቤት ባለ ፈንታ ሞላው ሃሴት አዝ፦ አቤት ምህረቱ ምህረቱ እሆሆ (3x) አቤት ቸርነቱ ቸርነቱ አሃሃ (3x) አቤት በጐነቱ በጐነቱ ኦሆሆ (3x) የሚሸከም በዕድሜ ዘመን የሚታደግ ከሰቀቀን ጽኑ አለት የሚያስመካ አማኑኤል አለኝ ለካ ከእንግዲህስ ለምን ልፍራ ጌታ እያለኝ የሚያኮራ ምህረቱን እደገፋለሁ ይህን አለት አምነዋለሁ አዝ፦ አቤት (3x) ይሄ ጌታ አቤት (3x) ምህረቱ አቤት ምህረቱ ምህረቱ እሆሆ (3x) አቤት ቸርነቱ ቸርነቱ አሃሃ (3x) አቤት ማፅናናቱ ማፅናናቱ ኦሆሆ (3x) አቤት በረከቱ በረከቱ ኦሆሆ (3x) አቤት ደግነቱ ደግነቱ ኦሆሆ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection