ይሁን እንጂ ይብዛለት ምሥጋና ሳላቋርጥ እሰዋለሁ ገና አይደክመኝም ሁሌ አመልከዋለሁ ለሕይወቴ ትርጉሟ ኢየሱስ ነው (2x) ተሰጥቼ አመልካለሁ በፈቃዴ አመልካለሁ በመንፈሴ አመልካለሁ በእውነትም አመልካለሁ በማለዳም አመልካለሁ በቀትርም አመልካለሁ በምሽትም አመልካለሁ በሌሊትም አመልካለሁ በዝማሬም አመልካለሁ በሽብሸባም አመልካለሁ በደስታም አመልካለሁ በዕልልታም አመልካለሁ አሞጋግሸው መቼ ጨረስኩና ገና አልጠገብኩም አቅርቤ ምሥጋና ባማረ ዜና እቀኝለታለሁ በገናዬን ይዤ ማልጄ እነሳለሁ አለብኝ ውለታው (8x) እንዴት (4x) እረሳለሁ እንዴት (4x) እረሳለሁ ኧረ እንዴት (4x) ዝም እላለሁ እንዴት (4x) ዝም እላለሁ የተደረገልኝ ምህረት ከአሰብኩት ከአይምሮዬ በላይ ነው የተደረገልኝ ቸርነት ከአሰብኩት ከአይምሮዬ በላይ ነው የተደረገልኝ በጐነት ከአሰብኩት ከአይምሮዬ በላይ ነው ገና ከፍጥረቴ የቁጣ ልጅ ነበርኩ (2x) ምህረት ተደርጐልኝ ከእግዚአብሔር ጋር ታረኩ (2x) ያጐበጠኝ ቀንበር ወደቀ ከላዬ (2x) አምሮብኝ ብታዩኝ በአምላኬ ዛሬ ቀና ብዬ (2x) በኃጥያቴ ሙታን እያለሁ ከእግዚአብሔር ምረት ተቀብያለሁ ለሆነው ነገር ምን እከፍላለሁ ቀንና ሌሊት እዘምራለሁ (2x) አሞጋግሸው መቼ ጨረስኩና ገና አልጠገብኩም አቅርቤ ምሥጋና ባማረ ዜና እቀኝለታለሁ በገናዬን ይዤ ማልጄ እነሳለሁ አለብኝ ውለታው (8x) ተሰጥቼ አመልካለሁ በፈቃዴ አመልካለሁ በመንፈሴ አመልካለሁ በእውነትም አመልካለሁ በማለዳም አመልካለሁ በቀትርም አመልካለሁ በምሽትም አመልካለሁ በሌሊትም አመልካለሁ በዝማሬም አመልካለሁ በሽብሸባም አመልካለሁ በደስታም አመልካለሁ በዕልልታም አመልካለሁ