ሰማያትን ሳይ ከዋክብትን የፀሐይ ድምቀት ግሩም ፍጥረትህ ምድርን ወብ አድርገህ ማበጃጀትህ አይጠገብም አቤት ጥበብህ አዝ፦ አንተን አደንቃለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ ለአንተ እዘምራለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ አእዋፍ በዛፎች ላይ ተደላድለው ሲያርፉ በማለዳ መዝሙር ሌሊቱን ሲገልጡ ብሩህ ልዩ ተስፋ ጥርት ባለው ሰማይ ትናንት ትናንት አልፎ አዲስ ቀን በቀን ላይ አዝ፦ አንተን አደንቃለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ አንተን አመልካለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ የፍጥረት ቀለም ድብቅ ውበቱ የሰማይ ርቀት የምድር ስፋቱ ግሩም ድንቅ ቤት ለሰው መቆያ ጌታ ያዘጋጀህ መልካም ማደሪያ አዝ፦ አንተን አደንቃለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ አንተን አመልካለሁ (3x) ስምረትን እያየሁ አድማስ ከሩቅ ሆኖ ፍጥረትን ሲታዘብ ደመና ከሰማይ አውቆ ሲሰበሰብ በዶፍ ዝናብ መሃል መብረቅ ሲያስተጋብ ፍጥረት ቤቱን አውቆ በስፍራው ሲገባ አዝ፦ አንተን አደንቃለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ አንተን አመልካለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ ጊዜ ጊዜን ሲወልድ ወቅቱ ሲለዋወጥ መልካም ፍሬ አበባ አዲስ ዘር ሲገለጥ ጭጋጉ ደመናው በድንገት ተገፎ ፀሐይ ስትፈነጥቅ ወቅቱ በወቅት አልፎ አዝ፦ አንተን አደንቃለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ አንተን አመልካለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ በውድቅት ሌሊት ታይቶ የማይጠገብ ከዋክብት ሲያበሩ ግርማቸው ሲነበብ ሰማይ እንደ ድንኳን አምሮ ተዘርግቶ እንዴት ደስ ያሰኛል ማየት ምድርን ሞልቶ አዝ፦ አንተን አደንቃለሁ (3x) ፍጥረትን እያየሁ ለአንተ ዘምራለሁ (2x) አንተን አመልካለሁ ሰማይን እያየሁ ኦ ሃሌሉያ ኢየሱስ ሥምህ ከፍ ከፍ ይበል ። እንደ አንተ ያለ ማን አለ? ሃሌሉያ!