Song Lyrics

ከአንተ ጋራ

Tesfaye Chala
Wetimedu Tesebiro Ameletiku
አዝ፦ ከአንተ ጋራ (3x) ኢየሱስ ከአንተ ጋራ ከአንተ ጋራ (3x) ውዴ ከአንተ ጋራ ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አላፈርኩም ከአንተ ጋራ (2x) ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አሸነፍኩኝ ከአንተ ጋራ (2x) የማይሸከሙት ለሰው የማይነግሩት ወይ በሆድ ደብቀው የማያባብሉት ሥጋት የማይገፋው የዚህ ምድር ጣጣ ትንሹን ሲሸኙት ትልቁ ሲመጣ አለፍኩት ሁሉንም ውዴ ከአንተ ጋራ አቀበት ቁልቁለት ሜዳና ተራራ ስወድቅ ያረሳኸኝ ስደክም ያነሳኸኝ በዚች አጭር ዕድሜ ስንቱን አሳለፍከኝ አዝ፦ ከአንተ ጋራ (3x) ኢየሱስ ከአንተ ጋራ ከአንተ ጋራ (3x) ውዴ ከአንተ ጋራ ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አላፈርኩም ከአንተ ጋራ (2x) ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አሸነፍኩኝ ከአንተ ጋራ (2x) የዚህ ዓለም ክፋት መውረድና መውጣት ነፍሴን ቀንና ሌሊት እያንከራተታት አቅም አጣሁ ብዬ ጉልበቴ ሲከዳኝ ስጮህ ሳለቃቅስ ፈልጌ የሚረዳኝ በእኩለ ሌሊት የመጣኸው ጌታ ደግመህ አስታጠከኝ ጉልበቴ ሲፈታ እቀኝልሃለሁ ክብር ይሁንልሕ በምንም በማንም እኔስ አልለውጥህ አዝ፦ ከአንተ ጋራ (3x) ኢየሱስ ከአንተ ጋራ ከአንተ ጋራ (3x) ውዴ ከአንተ ጋራ ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አላፈርኩም ከአንተ ጋራ (2x) ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አሸነፍኩኝ ከአንተ ጋራ (2x) ከእንግዲህስ አይሆንም ብዬ የዘጋሁት አምርሬ አልቅሼ አፈር ያለበስኩት ተስፋ የሌለበት የሞተው ነገሬ ልረሳው ስሞክር በጊዜ ቀብሬ አንተ ከሰማያት ወርደህ ስታልፍበት በሞት ፈንታ ሕይወት ብለህ ስታዝበት የሞተው ተነስቶ ሲሄድ አይቻለሁ ለተዓምራትህ ምስክር ሆናለሁ አዝ፦ ከአንተ ጋራ (3x) ውዴ ከአንተ ጋራ ከአንተ ጋራ (3x) ኢየሱስ ከአንተ ጋራ ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አላፈርኩም ከአንተ ጋራ (2x) ሸለቆው በውኃ ይሞላል የማይቻለው ይቻላል እኔ አይቻለሁ ስትሰራ አሸነፍኩኝ ከአንተ ጋራ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection