ኃያላን ከምድር ተሰብረው ሲወድቁ በራሳችው በትር እራሳቸው ሲያልቁ አንዱ አንዱን ሲተካው ዓለም ሲለዋወጥ የጀግና ሰው ዙፋን መንበር ሲገለበጥ አንተን ግን ጌታ ሆይ ሊደፍር ማን ቻለ ሥምህ በምድር ላይ እጅጉን አየለ ብንሰግድልህስ አቤት ያንስብሃል ጌታ ሆይ ክብርህን በዓይናችን አይተናል አዝ፦ ክበር አንተ ብቻ (3x) (ይገባሃል) ይገባሃልና ይገባሃልና ይገባሃልና (2x) ፈርዖን ሊያጠፋን ኃይሉን አዘጋጀ እንዲያው ላይሆንለት ብዙ ጦሩን ፈጀ አንተ ግን በድንገት ደርሰህ ድል አረከው ክብር የሚገባው ጌታ ሆይ ለአንተ ነው ዙፋንህ የፀና ሥምህ የገነነ ማን አለ እንደ አንተ የተመሰገነ ብንሰግድልህስ አቤት ያንስብሃል ጌታ ሆይ ክብርህን በዓይናችን አይተናል አዝ፦ ክበር አንተ ብቻ (3x) (ይገባሃል) ይገባሃልና ይገባሃልና ይገባሃልና (2x) ሥምህን ሊያጠፉት ብዙዎች ተነሱ ያለ የሌለውን ጦሩን አስገዝተው ሽር ጉድ ሲሉ በምድር ጥበብ ዕውቀት አንተ በሰራኸው ታይተው ሊነግሱበት አስበው ሲጥሩ ከላይ አየህና ክብርህስ ሲነካ መቼ ትውድና ክንድህን ዘርግተህ ገለባበጥካቸው እንደ ምድር ትቢያ በነነ ሥማቸው አዝ፦ ክበር አንተ ብቻ (3x) (ይገባሃል) ይገባሃልና ይገባሃልና ይገባሃልና (2x)