Song Lyrics

ሳልወድህ የወደድከኝ

Tesfaye Chala
Libarkew getayen Libarkew
ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥከኝ በከበረው ደም ገዝተህ እንዲያው ልጅህ ያረከኝ አበሳዬን አራከው ቀንበሬን ሰባበርከው (ፍቅርህ ለእኔ ልዩ ነው ስምህን ላሞጋግሰው) (2x) ኃጢአተኛሳለሁ ጽድቅ የማይገባኝ መርገሜን ወሰደው ኢየሱስ በደሙ አነጻኝ የከሰሰኝ ጠላት እግሬ ስር ወደቀ በረሃው ሕይወቴ ደረቁ ምንጭን አፈለቀ ለዚህ የሚያበቃ ጽድቅ እንኳን ሳይኖረኝ በሰማዩ ስፍራ በቀኙእንዲሁ አከበረኝ ምህረቱ ብዙ ይሄ ታላቅ ጌታ ከእኔ ጋር ሆናችሁ በዜማ አክብሩት በልልታ አዝ ሳልወድህ የወደድከኝ የዕዳ ጽህፈቴን በደሙ ደምስሶ ጠላቴን በእጄ እረግጦ ሰጠኝ አሳልፎ ጽኑ ስልጣን አለኝ የአምላክ ልጅ ሆኛለሁ የፈታኝን ጌታ ተፈትቸ አከብረዋለሁ አዝ ሳልወድህ የወደድከኝ ለዚህ የሚያበቃ ጽድቅ እንኳን ሳይኖረኝ በሰማዩ ስፍራ በቀኙእንዲሁ አከበረኝ ምህረቱ ብዙ ይሄ ታላቅ ጌታ ከእኔ ጋር ሆናችሁ በዜማ አክብሩት በልልታ አዝ ሳልወድህ የወደድከኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection