አንተን ጠርቶ ማን አፈረ ተማምኖብህ ማን ከሰረ የተዘጋውን ትከፍታለህ የታሰረውን ትፈታለህ የታመመውን ታድናለህ የሞተውን ታስነሳለህ (ስልጣን ያንተ የእኔ ጌታ ስልጣን የአንተ ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ ስልጣን የአንተ) (2x) ባሕር መክፈል ትችላለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ በር ሲዘጋ ትከፍታለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ የችግረኛውን ጩኸት የምትሰማ የክፉ ቀን ወዳጅ ብርሃን በጨለማ እስከዛሬስ ማንን ጥለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ ቢመኩብህ ታስመካለህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ (ቢመኩብህ ታስመካለህ) (4x) አዝ አንተን ጠርቶ መርከቢቱ ስትናወጥ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ ሰጠምን ሲሉ ሲንቀጠቀጥ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ በድንገት ብቅ ብለህ ማዕበሉን ገሰጽከው ለአምላክነትህ ኢየሱስ ፍጥረት ምስክር ነው እኛንም ከሕይወት ማዕበል ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ ስንት ጊዜ አሳረፍከን ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ (ስንት ጊዜ እረዳኸን ስንት ጊዜ አሳረፍከን) (2x) አዝ አንተን ጠርቶ የሞተው ሲታዘዝልህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ ታላቁ ሰው ሲሰግድልህ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ በዝች አጭር ዕድሜ ብዙ ጊዜ አይተናል ሳይወድ በግዱ ፍጥረት ለአንተ ይገዛል ማንስ ሊቆም ከአንተ ጋራ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ ለሚያምኑበት የሚያኮራ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ (ለሚያምኑበት የሚያኮራ) (4x) አዝ አንተን ጠርቶ