(ልባርከው ጌታዬን ልባርከው) (4x) በሰማዩ ስፍራ ባረከኝ የረገጥኩትን አወረሰኝ ታዲያ ምን ይሰጣልለጌታ እስኪ ከፍ አርጉልኝ በልልታ የነገረኝን በሙሉ እስከሚያደርግልኝ ታምኖ ለክፉ ቀን መሸሸጊያ በሃሩር ጥላዬ ሆኖ ሲጠማኝ ምንጭ አፈለቀ ሲርበኝ ደግሞ አጐረሰኝ ሰው ዓይንህ ለአፈር ሲለኝ ኢየሱስ አንዴም ሳይሸሸኝ እንደበደሌ አልከፈለኝ ምህረቱ ስለእኔ በዝቷል በነፍስና በሥጋዬ በረከቱ ቤቴን ሞልቷል እንዴት ታዲያ ዝም ልበል ይህንን ሁሉ አይቼ ልስገድ ልውደቅ በግንባሬ ቤቱ ማደሪያው ገብቸ አዝ ልባርከው ጌታዬን በደሌ በፊቱ በዝቶ ያለቀ የሞትኩ ሲመስለኝ የጠላቴማስፈራራት ጩኸቱ ሲያርበደብደኝ በዘመርኩበ አንደበት ሙሾ ለመውረድ ስዳዳ የሞትን ወሬ ሰምቸ ለነፍሴ ሞትን ላረዳ ስዋከብ ከዚህ ወደዚያ ጭንቀቴን አይቶ ደረሰ የተዋጋኝን ተዋጋው እቅዱን አፈራረሰ ዛሬማ በኮረብታ ላይ ቆሜ ምሥጋና እዘምራለሁ ሰው ያደረገኝን አምላኬንበዜማ እባርካለሁ አዝ ልባርከው ጌታዬን በሰማያዊ በረከት በመንፈስ ባርኮ ባረከኝ የምድሩን አላጣሁም ይልቁን አትረፈረፈኝ ሳይሰለች የተሸከመኝ ቀን በቀን ቤቴን ባረከው ዓለም የነፈገችኝን ኢየሱስ አጥፍ አረገው የሱስን ብሎ ወዝ አጣ ያሉዛሬ ይሄው አፈሩ ጌታ ሞገሴ መሆነን በአፋቸው መሰከሩ ወጥመድ ቢዘጋጅልኝም ኢየሱስ እየቀደመ ሕይወቴን በረከት ሞላውደረቅ በትር ለመለመ አዝ ልባርከው ጌታዬን እናንተም አንደኔው ጌታ ቀን በቀን የባረካችሁ በተሰደዳችሁበት ምድር እጅግ ያበዛችሁ የገዛችሁን ኢየሱስ ከእግራችሁ ላስገዛላችሁ ጂራት ስይሆን እንደ ቃሉ የሁሉ እራስ ያረጋችሁ እስኪ እናንተው ንገሩኝ ለኢየሱስ ምን ይከፈላላ ወደር ለሌለው ምህረቱ ምን ምላሻ ምንስ ይሰጣል ከአድማስ አድማስ ባሻገር ሙገሳ ክብር ሙገሳ ይድረሰው ፍጥረት ሁሉ ይህን ጌታ በአንደበቱ ይቀድሰው አዝ ልባርከው ጌታዬ