Song Lyrics

በራችንን ደጁን ዘግተን

Tesfaye Chala
Libarkew getayen Libarkew
(ልባርከው ጌታዬን ልባርከው ልባርከ እየሱሴን ልባርከው) (2x) በሰማዩ ስፍራ ባረክኝ የረገጥኩትን አወረሰኝ (ታዲያ ምኔን ልስጠው ለጌታ እስኪ ከፍ አርጉልኝ በልልታ) (2x) የነገረኝን በሙሉ እስከሚያደርግልኝ ታምኖ የክፉ ቀን መሸሸጊያ በሃሩሩ ጥላ የሆነው ሲጠማኝ ምንጭ አፈለቀ ሲርበኝ ደግሞ አጐረሰኝ ሰው ዓይንህ ላፈር ሲለኝ ኢየሱስ አንዴ ሳይሸሸኝ እንደበደሌ አልከፈለኝ ምህረቱ ስለእኔ በዝቷል በነፍስና በሥጋየ በረከቱ ቤቴን ሞልቷል እንዴት ታዲያ ዝም ልበል ይህንን ሁሉ አይቸ ልስገድ ልውደቅ በግንባሬ ማደሪያው ቤቱ ገብቸ አዝ ልባርከ ጌታዬን በደሌ በፊቱ በዝቶ ያለቀ የሞትኩ ሲመስለኝ የጠላቴ ማስፈራራት ጩኸቱ ሲያርበደብደኝ በዘመርኩበት አንደበት ሙሾለመውረድስዳዳ የሞትን ወሬ ሰምቸ ለነፍሴ ሞትን ላረዳ ስዋከብ ከዚህ ወደዚያ ጭንቀቴን አይቶ ደረሰ የተዋጋኝን ተዋጋው እቅዱን አፈራረሰ ዛሬማ በኮረብታ ላይ ቆሜ ምሥጋና እሰዋለሁ ሰው ያደረገኝን አምላኬን በዜማ እባርካለሁ አዝ ልባርከው ጌታዬን በሰማያዊ በረከት በመንፈስ ባርኮ ባረከኝ የምድሩንም አላጣሁም ይልቁን አትረፈረፈኝ ሳይሰለች የተሸከመኝ ቀን በቀን ቤቴን ባረከው ዓለም የነፈገችኝን ኢየሱስ እጥፍ አረገው ኢየሱስን ብሎ ወዝ አጣ ያሉኝዛሬ አፈሩ ጌታ ሞገሴ መሆኑን በአፋቸው መሰከሩ ወጥመድ ቢዘጋጂልኝም ኢየሱስ እየቀደመ ሕይወቴን በረከት ሞላው ደረቅ በትር ለመለመ አዝ ልባርከው ጌታዬን እናንተም እንደኔው ጌታ በቀን በቀን የባረካችሁ በተሰደዳችሁበት ምድር እጅግ ያበዛችሁ የገዛችሁን ኢየሱስ ከግራችሁ ያስገዛላችሁ ጂራት ሳይሆን እንደቃሉ የሁሉ ራስ ያረጋችሁ እስኪ እናንተው ንገሩኝ ለኢየሱስ ምን ይከፈላል ወደር ለሌለው ምህረቱ ምን ምላሽምንስ ይሰጣል ከአድማስ እስከ አድማስ ሙገሳክብር ሙገሳ ይድረሰው ፍጥረት ሁሉ ይህን ጌታ በአንደበቱ ይቀድሰው አዝ ልባርከው ጌታዬን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection