ገናና የእኛ ኢየሱሱ አቻ አይገኝለት እንደሞተ አልቀረም ከቶ አለ በሰማያት ማን ይቃወመናል ዛሬስ በደሙ ዋጅቶናል ትንሴኤውን ልናወራ (በገና አንስተናል) (2x) (ምሥጋና) (3x) ለሆነው ገናና (ዕልልታ) (3x) ድል ላረገው ጌታ ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ የዕዳውን ጽህፈት በደሙ አስወግዶ ምስኪን መስሎ መቶ ዲያብሎስን ቀጣ በጨለማ ላሉ አዲስ ፀሐይ ወጣ አዝ ገናና የእኛ ኢየሱስ ጐስቋላና ድሃ ምስኪን የህማም ሰው ባየነውም ጊዜ ደም ግባት የሌለው ፍቅር ኃይሉ ሆነች ድካሙ በረታ ማንም ሳያግዘው ዲያብሎስን መታ አዝ ገናና የእኛ ኢየሱስ የጣር የሰቆቃው ጩኸቱ ሲሰማ መከራው በዝቶበት ቢመስልም ደካማ ምድር አልቻለችም ሞትን ፈነቀለ ተስፋ ለቆረጡ አዲስ ዘር በቀለ አዝ ገናና የእኛ ኢየሱስ ስሙም ድንቅ መካር የሰላም አለቃ ሞትና ርግማንም ስቃዩ አበቃ ገናና ገናናገናና ነው አሱ በሆታ በልልታ ስሙን አሞግሱ አዝ ገናና የስኛ ኢየሱስ