(እወድሃለሁ ጌታ እወድሃለሁ የሱስ) (2x) በኃጢአቴ ሙታን በነበርኩ ጊዜ ሳላይህ ያየኸኝ ሳላውቅህ አውቀኸኝ ከክርስቶስ ጋራ ሀይወትን ሰጠኸኝ እኔ ምን እላለሁ ላመስግንህ ጌታ እጄን ልዘርጋ እንጂ አንተ የፍቅር ጌት ምረትህ የማያልቅ ፍቅርህ አያረጂ ከአስፈሪው ነበልባል እውድሃለሁ ጌታ ከገሃነብ ዳንኩኝ እወድሃለሁ የሱስ እኔም እንደ ጻድቃን እውድሃለሁ ጌታ ጸድቀሃል ተባልኩኝ እወድሃለሁ ጌታ በኃጢያቴ ምክንያት የሞትኩኝ ነበርኩኝ እኔም በእግዚአብሔር በአምላኬ ታሰብኩኝ የመርገም ጨርቄን ከላዬ ገፈፈው ጽድቅን አለበሰኝ (የሚከሰኝ ማን ነው) (2x) አዝ እወድሃለሁ ጌታ እግዚአብሔርም ከወደደን ክትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በኃጢአታችንና በበደላችን ሙታን በነበርን ጊዜ ከክርስቶስ ኢየሱሱ ጋር ሕይወትን ሰጠን ሰው ዞር ብሎ እያየኝ ቢሆንማ ኑሮ ምህረት በሰው እጂ እንኳን ለጽድቅ እንኳን ለሌላው ሰው ለራሴም አልበጂ ዓይኑ እንዳየች ሳይሆን ጀሮው እንደሰማች ሳይፈርድ አጸደቀኝ አረ ይገርማል አረ ይገርማል ሰዎች እኔንም አዳነኝ የማይገባኝን እወድሃለሁጌታ የሕይወትን አክሊል እወድሃለሁ የሱስ በነጻ ሰጠኸኝ እወድሃለሁ ጌታ ስምህ ከፍ ይበል እውድሃለሁ የሱስ አዝ (እወድሃለሁ ጌታ እወድሃለሁ የሱስ) (2x)