Song Lyrics

ብቻውን ተዓምር የሚሰራ

Tesfaye Chala
Libarkew getayen Libarkew
(ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ ችግረኛን የሚታደግ እንቆቅልሽ የሚፈታ ኢየሱሱ የኝ ጌታ) (2x) ጠላት ሲሽቀዳደም ሊመታን በጡጫ ቅጥሩን ሰበረልን ሆነልን ማምለጫ እንናገር ብንል ብዙ እናወራለን በዝች አጭር እድሜ ምረቱን ስላየን በዝች አጭር ዘመን ማዳኑን ስላየን አዝ ብቻውን ተዓምር ኃጢአታችን በዝቶ ስንባዝን በዓለም ሕይወት ሆነን የሱስ ሊያኖረን ዘለዓለም ምን እንመልሳለን ከምሥጋና ሌላ (በጭንቃችን ስዓት ለሆነን ከለላ በጭንቃችን ስዓት ለሆነን ከለላ) አዝ ብቻውን ተዓምር የአናብስትን አፍ ጥርስ እየሰበረ ከክብር ወደ ክብር እያሸጋገረ በደመናው አምድ ዘወትር ይመራናል ከኢየሱስ ጋር ሆነን አረ ምን ጐሎናል ከኢየሱስ ጋር ሆነን አረ ምን ጐሎናል አዝ ብቻውን ተዓምር ጠላት ሲሽቀዳደም ሊመታን በጡጫ ቅጥሩን ሰበረልን ሆነልን ማምለጫ እንናገር ብንል ብዙ እናወራለን በዝች አጭር እድሜ ምረቱን ስላየን በዝች አጭር ዘመን ማዳኑን ስላየን አዝ ብቻውን ተዓምር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection