የአምላኬን ቤት ጠላት ሲወርሰው ሰውም ለራሱ መኖር ሲመቸው ጠባቂው ሸሸ ሁሉም ሲተኛ መንጋው ሲበተን ጠፍቶ እረኛ እንጀቴን ልሰር ምግብ አልብላ ነግ ይሆናል ፍርዱ በኋላ የአምላኬ ባሮች አስኪ ተነሱ ለፈረሰው ቅጥር ኑና አልቅሱ ልመለስ ልግባ ወደ እልፍኝህ ልንቃና ልማልድ ተግቸ የደከምኩ ያረጀሁ ቢመስለኝ በአምላኬ እኔስተስፋ አልቆርጥም ዓይኖቸ ፈዘው በቅጡ ሳላይ ጠላት ሲሳሳቅ በአምላኬ ቤት ላይ ከተኛሁበ ድንገት ስነቃ ቅናቱ በላኝ ሆነኝ ሰቆቃ ጉልበቴን ጠላት በልቶት ቢዝልም መውደቄን ሰምቶ ቢጠቋቆምም ወድቄ አንቀርም ደግሞ እነሳለሁ የአምላኬን ቅጥሩን አሳምራለሁ አዝ ልመለስ ማን ወድቆ ቀርቷል ሳያንሰራራ የጠላቱንስ ጡጫ እንደፈራ ባለቀ ስአት መድረስ የሚያውቀው ታማኙ አምላኬ ከእኔ ጋራ ነው የጠላቱን ቤት መቶ ያፈርሳል የእርሱ የሆኑትን ጌታ ያጠራል ጸሎቴን ሰምቶ ይጐበኘኛል የሱስን ይዤ ምን ያሰጋኛል አዝ ልመለስ በአባቴ ቤት ሸቀጡ በዝቶ ሁሉም ሊነግድ ያለውን አምጥቶ መደቡን ሰርቶ ሰው ቢመቻችም ኢየሱስ ይሄንን ዝም ብሎ አያይም ጌታ ጂራፉን ይዞ ይነሳል የቤቱን ጉድፍ ጠርጐ ይወጣል የሳቀ ጠላት በተራው ያፍራል የክብሩ ቤት ግን ገና ያበራል አዝ ልመለስ