Song Lyrics

ክብር ለሆነን ጌታ

Tesfaye Chala
Libarkew getayen Libarkew
ክበር የሆነን ጌታ ሞገስ የሆነን ጌታ ብቃት የሆነን ጌታ በጉድለታችን ፈንታ ክንዱን በዘመናችን በዓይናችን አይተነዋል መልካም እረኛ ኢየሱስ እስከዛሬ ረድቶናል በዘመን በአመታት መሃል የሚገዳደረው የታል ብቻውን ድንቅ እየሰራ የሚኖር እንደተፈራ ለእኛም ይሄው ሞገስ ሆነን ባሕሩን ከፍሎ አሻገረን ችግራችንን እረሳነው በኢየሱሱ ስንቱን አለፍነው አዝ ክበር የሆነን ጌታ ስንቱን ተሻገርንአለፍን በምሥጋና ሆ እያልን ስንቱስ ከእግራችን ወደቀ በኢየሱስ እይደቀቀ ዘመን ሲያልፍ ዘመን ሲተካፍሬያችንአብቦ ፈካ የረገጥነውን ወረስን እለት እለት አማረብን አዝ ሞገስ የሆነን ጌታ በምድረ በዳ በረሃ የሚያረካ ውኃ ሆነን አልሰለቸን የእኛ ጌታ እንደቃሉ ተለመነን በመከራ ቀን ሰቀቀን ተማምነን ስሙን ስንጠራ ደረሰልን በስአቱ ኢየሱስ ጌታ የሚያኮራ አዝ ክብር የሆነን ጌታ ሸንጐ በእኛ ላይ ሲማከር ዲያብሎስ ሊያጠፋን ሲጥር ማነው ደርሶ የታደገን መርከብ ሆነን ታሪክ ይናገር ብዙ ብዙ ነው እኛስ ያለፍነው በእግራችን ስር ወድቆ ጠላት ጭንቅላቱን ረገጥነው አዝ ክበር የሆነን ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection