አዝ፦ ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (2x) ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x) ለቅሶውን የሚሰማው አጥቶ ከሰው ህሊና ተረስቶ ደክሞ በዓልጋ እየማቀቀ ዕድሜው ከምኑ አለቀ የተባለው ያ ሰው ዛሬ ይሄው ቆሟል አስኪ እዩት አልጋውን በትከሻው ይዟል ይህን የአደረገው ክብሩ የገነነ ኢየሱስ ይባረክ ደሃን የተለመነ አዝ፦ ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (2x) ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x) አሳዳጅ እጅግ ጨካኝ ሰው አገር ምድሩ ሁሉ የሚያወቀው ጌታን እምርሮ ሚጠላ ለሕዝብ . (1) . የቀና ድንገት ጌታ ደርሶ ይህን ሰው ሲነካው ሥሙ ጳውሎስ ሆነ ከዚያ ማን ይቻለው ወንጌልን በምድር በስልጣን ሰበከ ጀግና ነው ኢየሱስ ጀግናውን ማረከ አዝ፦ ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (2x) ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x) አፈር ለብሶ የሸተተ . (2) . ኑሮው ተከተተ አልዓዛር ወየው በቃለት ከኃጢአት ተለየ በሞት ስትል ማሪያም አዝና እንባዋን እየዘራች ምነው ኢየሱስ በዚህ ቢኖር ኖሮ እያለች ተስፋ ቆርጣ ደክማ አልዓዛርን ጠራው ኢየሱስ በዚያ ሲሄድየድል ብርሃን በራ አዝ፦ ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (2x) ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x) ከመንገድ ወድቆ ሲለምን አካሉ ሁሉ ሲማቅቅ . (3) . ደክሞ አይበላ ዘመኑን ሁሉ ሲጉላላ ቀኑ ደረሰና ኢየሱስ መጣለት ደጋግሞ እየጮኸ ተጣራ በእምነት ከለማኙ . (4) . ኢየሱስ ጌታ ነው ታሪኩን ለወጠ አዝ፦ ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (2x) ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x) በሃኪም ገንዘቧን ጨርሳ ሃፍረት እንደ ሸማ ለብሳ ከሰው ከሃገሩ እየራቀች አስራ ሁለት ዓመት ማቀቀች የምስኪኖች ተስፋ በመንደሩ አለፈ ሊጐበኛት ፈቅዶ ሸክሟን አራገፈ ኧረ ምን ይባላል ምንስ ይመለሳል እውነትም ፍቅር ነው ለምስኪን ይደርሳል አዝ፦ ስምህ ይባረክ ዘለዓለም ስምህ ይባረክ (2x) ተመስገን ኢየሱስ/ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ ከአንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆኛለሁ (2x)