Song Lyrics

ጻድቅ ግን በእምነት

Tesfaye Chala
Bamare Kine
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ ኖህ በምድረ በዳው መርከብን አበጀ አብረሃም እርስቱን ከነዓንን ወረሰ ሳራም በእምነቷ ኃይሏ ተመለሰ አዝ፦ ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ይረዳል የተስፋውን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና ደካሞች በእምነት ጉልበታችሁ ይጽና (2x) ነፍሱ ፍፁም ደክማ ትንፋሽ ተሰውሮ የሚታይ መመኪያ ከአፈር ተቀብሮ ሥጋ ደግሞ ዝሎ ሞት ሽታ ሲሸተው ጻድቅ ግን በእምነት ከክርስቶስ ጋር ነው አዝ፦ ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ይረዳል የተስፋውን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና ደካሞች በእምነት ጉልበታችሁ ይጽና (2x) ባሕሩን በበትር አሻግሮ የከፈለ ውሃን እንደ ግድግዳ ገትሮ ያቆመ ዝናብን ኤልያስ በእምነት ከለከለ እስራኤል በአምላኩ ጉልበቱ አየለ አዝ፦ ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ይረዳል የተስፋውን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና ደካሞች በእምነት ጉልበታችሁ ይጽና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection