Song Lyrics

እረኛን ይቀባል

Tesfaye Chala
Bamare Kine
ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ ሳኦልም አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክ ሁን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው ሳሙኤልም ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጐች ጩኸትና የበሬዎች ግሳት ምንድን ነው? አለ ሳኦልም ህዝቡ ለአምላክህ ይሰውአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጐችና በሬዎችን አድነዋቸዋልና አማሌቃዊያንም አምጥተዋቸዋል የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ እስከመቸ ድረስ ለሳኦል ታለቅሳለህ ውረድ ቤተልሔም በቀንድ ዘይት ሞልተህ ከልጆቹ መሃል አዘጋጅቻለሁ ወደ እሰይ ቤት ግባ ነገ እሱን ቀባለሁ ሲለኝ አግዚአብሄር ፈራሁ ተደናገጥሁ ሳኦል እንዳይሰማ ብዬ እጅጉን ሰጋሁ አንዲት ጊደር ይዤ ጌታዬ እንዳዘዘኝ ጠራሁት እሰይን ልጆቹን እንዲያሳየኝ በእውነት መልኩ ያማረ ቁመናው ሸበላ ወደእኔ የተጠጋ ኤልያብ ነው ለካ እግዚአብሔር ሚቀባው በፊቴ ይህ አለ ለእስራኤል ንጉሥ ኧረ እፎይ ተገኘ ብዬ በውስጤ አስቤ ልቀባው ስጠጋ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ አትቸኩል በል ረጋ ሰው ፊትን እንደሚያይ እኔ አላይምና በዓይኔ ፊት ቀሏል አልያብን አትቀባ (2x) ሌሎችም ሰባቱ አለፉ በፊቴ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ አልመረጥኩም እኔ ልጆቹም አለቁ ማን ይሆን የቀረው የሚቀባው የታል ሰዉ ግራ ገባው የቀረ የለም ወይ እነዚሁ ናቸው እስኪ እሰይ ልጆችህን በደንብ ቁጠራቸው ገና ታናሽ አለ በጐች ይጠብቃል አለኝ መለሰና ሥሙ ዳዊት ይባላል (2x) ተጠርቶ መጣና በእኔ ፊት ቆመ እግዚአብሔር አየው ዓለኝ ቀባው ሂደህ የአምላኬ መንፈስ ወደደው አረፈበት ዳዊት ያ እረኛው በእውነት አማረበት እግዚአብሔር ለካስ መቼ ፊትን ያያል ልቡን ከወደደ እረኛን ይቀባል እኔም ታሪክ አለኝ የዳዊትን መሳይ አምላኬ ከትቢያ ከአመድ ላይ ሲያነሳኝ እግዚአብሔር ለካስ መቼ ፊትን ያያል ልቡን ከወደደ ምስኪኑን ያከብራል እኔም ታሪክ አለኝ የዳዊትን መሳይ አምላኬ ከትቢያ ከአመድ ላይ ሲያነሳኝ በሰው ዓይን ሲታዩ ዓይን የሚሞሉ ትከሻቸው ሰፊ ቁመናቸው ብቁ አልጠፉም ብዙ አሉ አገሩን ሞልተዋል በጌታ አይን ፊት ታዲያ መች ከብረዋል ለምን እንደወደደኝ በውል ባይገባኝም ስለእራሴ ማውቀው ውብ ታሪክ የለኝም እንደ እስራኤል ድፍረት ነበርኩ እራቁቴን ኢየሱሴ መጥቶ ጸጋ ባያለብሰኝ (2x) እግዚአብሔር ለካስ መቼ ፊትን ያያል ልቡን ከወደደ እረኛን ይቀባል እኔም ታረክ አለኝ የዳዊትን መሳይ አምላኬ ከትቢያ ከአመድ ላይ ሲያነሳኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection