አዝ፦ ውዴ (3x) ኢየሱስ (3x) ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ (2x) አስራ ሁለት ዓመት ደም እየፈሰሰኝ ተነጥዬ መኖር ሰው እንኳን እራቀኝ ከእንግዲህስ ወዲያ ተስፋዬ ምንድን ነው ዕድሜዬ በሙሉ በለቅሶ ሊያልቅ ነው ብዬ ደምድሜ ሃሳቤን ስጠብቀው ፍጻሚዬን ድንገት ብርሀን ወጣልኝ አዳኜ ኢየሱስ መጣልኝ አዝ፦ ውዴ (3x) ኢየሱስ (3x) ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ ግርግሩ በዝቶ የሚጋፋው ሰው አዳኜ ኢየሱስን እንዴት ላግኘው ተስፋ ባለመቁረጥ እያተንኳተትኩኝ እጄን ሰደድኩና ቀሚሱን ነካሁኝ ነካ ባደርገው ነካኝ ኃይልም ወጣና ዳንኩኝ ታዲያ ምን ልበል ይህን ጌታ አመስግኑልኝ በልልታ አዝ፦ ውዴ (3x) ኢየሱስ (3x) ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ ዘመናት አለፉ ሆኜ በጭንቀት ለደሜ ማድረቂያ ጠፍቶ መድሐኒት ማንም ማይጠጋኝ እርኩስ ናት ተብዬ አሁንስ መረረኝ ገላግለኝ ጌታዬ ብዬ ሞቴንም ስናፍቅ በሽታዬ አርጎኝ ድቅቅ መሲሁ መጣልኝና አቆመኝ ፈወሰኝና አዝ፦ ውዴ (3x) ኢየሱስ (3x) ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ ትድናለች ብሎ ኧረ ማን ገመተኝ ሁሉም በሩቅ ሲሸሽ ጀርባውን ሲሰጠኝ አስታማሚ አጥቼ የሚደግፈኝ ኢየሱስ ሲጐበኘኝ በዛ ሚያጅበኝ የሸሹኝ ሁሉ አቀፉኝ የናቁኝ ሁሉ አከበሩኝ መሸማቀቄም ቀረልኝ ኢየሱስ ይመስገንልኝ አዝ፦ ውዴ (3x) ኢየሱስ (3x) ምህረትህን አይቻለሁ አወራለሁ ምሕረትህን አይቻለሁ ዘምራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ አወራለሁ ማዳንህን ቀምሻለሁ ዘምራለሁ