ፊትህ እንደ ፀሐይ ያበራል እንደብዙ ውሆች ድምጽህም ያስፈራል ግርማህየደመቀ ሞገስህ ልዩ ነው እግርህ ስር ወድቄ እሰግድልህ አለሁ አልፋና ኦሜጋ የዘለዓለም ጌታ ሞትን ድል ያረገ ኃጢአትን የረታ ከወገን ከቋንቋህዝቦችን የዋጄ ለአምላኩ መንግሥት ካህናትያበጀ (ሰባቱን መጽሃፍትማህተም የፈታ ውበትህ ያማረ የይሁዳ አንበሳ) (2x) አዝ ፊትህ እንደ ፀሐይ ምስኪን ሆነህ መተህ ምስኪኑን ያከበርክ ደሃ ሆነህ መተህ ደሃን ያበለጸክ በደዌ ተመተህ ህምሙን የፈወስክ ኃጢአትን ለብሰህ ሃጢያኑን ያነጻህ (በከበረው ኃይልህ ባለድል ያረከን አንተ አትጠገብም ኢየሱስ ተመስገን) (2x) አዝ ፊትህ እንደ ፀሐይ ማምለጫ ቀዳዳ መሹለኪያ ሲጠፋ ጐዳናውእጅግ ጠቦ ሰው ሁሉ ሲጋፋ ችግር መፍታት አንተ ልማድህ ነውና መጽሃፉን ገልጽህ ማኅተሙን ፈታህ ጌታችን(ኢየሱስ) ተባረክ ባለግርማ ሞገስ ዙፋንህ ከፍ ይበል በዓለም ሁሉ ንገሥ አዝ ፊትህ እንደ ፀሐይ