Song Lyrics

ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው

Tesfaye Chala
Bamare Kine
ስምህ እንድ ሚፈስ ዘይት ነው ጌታ ሆይ መልካም መዓዛ አለው ውዴ ሆይ መልካም መዓዛ አለው ጌታ ሆይ ስምህን ጠርተን ተፈውሰናል ካለብን ደዌ ነጻ ወጥተናል ጅማታችንን ስምህ አራሰው ልባችን ሞልቷል ሃሌሉያ ነው ስለዚህ ጌታ ተመስገንልን አፍቅረንሃል ከውስጥ ከልብ ጎልማሳነታችንም ታድሷል በስምህ ብርታት ነጻ ወጥተናል አይምሮ አርሶ ከልብም አልፎ ያለ ሁኔታ ተድላን አልብሶ የሚጣፍጠው ሥምህ ቁልፍ ነው ደናግል ለአንተ በፍቅር ናቸው ሌሊት በምሽት ከእንቅልፍ ተነስተን ስንበረከክ አንተን ፈልገን ስምህን ጠርተን እፎይ እረካን ኢየሱስ ጌታ ማን ይመስልሃል ማድጋችንን ዘይትህ ሞላው ያንን ስምህን ታምነን ስንጠራው ባዶ ነበር ማስሮ ዕቃችን ገና አሁን በአንተ አገኘን ለጎረቤትም ተርፏል ሰላምህ ከእኛም አልፎ ከደናግልህ እነሆ ምንልህ የምንሰጥህ የለንምና ከፍ ይበል ስምህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection