Song Lyrics

ያ ሁሉ አለፈና

Tesfaye Chala
Bamare Kine
አዝ፦ እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን (2x) ምሥጋናዬ ይህ ነው ምሥጋናዬ አሰዋለሁ ዛሬ በኮረብታ ቆሜ ነጻ ወጥቼ ነጻ ሰው መሆን ችያለሁ በክርስቶስ ዛሬ ትልቅ ተብያለሁ የናቁኝም ያኔ አንቅረው የተፉኝ ጐንበስ አሉ ጐንበስ ጌታ አክብሮኝ ሲያዩኝ አዝ፦ እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን አሁን ይኸው እንዲህ እንዲህ አምሮብኛል አፌም በዝማሬ በዘይት ታብሷል ማንም አልጠበቀኝ እኔን ለቁም ነገር ጌታ ሲያረገው ግን ማነው የሚናገር ምስኪኖች ሆይ በርቱ ጌታ አይጥላችሁም/ሰውን አይጥልም ምስክር ነኝ እኔ በዓይኔ ስላየሁኝ (2x) አዝ፦ እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን ያኔ ያሰብኩት ሁሉ ወደ ገደል ገብቷል አሁን በሕይወቴ ዛሬ አካሌ ቆሟል ወገኖችም በቃ ብለው ነበር በቃ በሃያሉ ኢየሱስ ከመቃብር ወጣሁ እግሬም እንደዋላ አግሮች በርትተዋል አፌም በዝማሬ በዘይት ታብሷል አዝ፦ እንደማያልፍ የለም ያሁሉ አለፈና የሰቆቃው ዘመን በደስታ ተተካ አሜን አንገቴን ደፍቼ የሰው ፊት ፈርቼ ያለፍኩበት ዘመን ዘለፋ ጠግቤ አቤት በቃ ሲለኝ ጌታ ወደ ገደል ገባ የጐበጠ አንገቴ ለምሥጋና ቀና አሜን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection