Song Lyrics

ባማረ ቅኔ

Tesfaye Chala
Bamare Kine
አዝ፦ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ለሰው የማይቻለው ለእግዚአብሔር ይቻላል እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ፍፁም አላፍርም ባዳነኝ ጌታ አይቻለሁና በዐይኔ ያስጨነቀኝን ሲመታ ነገር ባይሞላ ባይሳካ ኢየሱስ ምን ይሳነዋል ከሞተው አንበሳ ሆድ ውስጥ ጣፋጭ ጣፋጭ ማር ያወጣል (2x) አዝ፦ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ለሰው የማይቻለው ለእግዚአብሔር ይቻላል ለምን ልጐሳቆል ልዘን ለምንስ ልቆዝም በእንባ ተዓምር ያስለመደኝ አምላክ መቼ ክንዱ ደከመና በታሰርኩበት ወህኒ ውስጥ ሆ እያልኩኝ እዘምራለሁ የጠላቶቼን ደጅ በእምነት በዝማሬ አፈርሳለሁ (2x) አዝ፦ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ለሰው የማይቻለው ለእግዚአብሔር ይቻላል ውድቀቴን ጠላት ሰምቶ ከበሮ ተይዞ ሲጨፍር አምላኩ ጥሎታል ዛሬስ ተብሎ አባጅ ሲነገር ሰው የማይጥል ጌታ አምላኬ ኃያል ክንዱን ሲዘረጋ ጠላቶቼ ሁሉ አለቁ በአንዲት የአህያ መንጋጋ (2x) አዝ፦ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ለሰው የማይቻለው ለእግዚአብሔር ይቻላል ሰላሙን ሞልቶ አባቴ በመስቀሉ ስር አሳረፈኝ ወደ ክብሩ ልጁም መንግሥት በታላቅ ፍቅሩ አፈለሰኝ ልጁን ለእኔ የሰጠ አምላክ ሌላ ምን ምን ይሳነዋል ባዶ ሸለቆዬ ሞልቶ ተርፎ ለአገር ሁሉ ይፈሳል (2x) አዝ፦ ባማረ ቅኔ ለኢየሱስ ምሥጋና ቃሉን የሚያደርግ ድንቅ አምላክ ነውና ደመናም ባላይ ሸለቆው ይሞላል ለሰው የማይቻለው ለእግዚአብሔር ይቻላል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection