አዝ፦ የመስቀሉ ፍቅር (4x) የመስቀሉ ፍቅር (4x) ለእኔ ነው መንክራተቱ መስቀል ላይ ውሎ መሞቱ ያኔ የፈሰሰው ደሙ አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ እንደሚታረድ በግ ዝም ያለው ግርፋት ስቃዩ ለእኔ ነው ሞቴን የሞተልኝ በጐልጐታ ውርደቴን ተዋርዶ ክፉን መታ በሕይወት አለሁኝ ዛሬም በዚህ ጌታ አዝ፦ የመስቀሉ ፍቅር (4x) የመስቀሉ ፍቅር (4x) ለእኔ ነው መንክራተቱ መስቀል ላይ ውሎ መሞቱ ያኔ የፈሰሰው ደሙ አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ ክቡር ሆኖ ሳለ የከበረ ጌታዬ ስለእኔ ራሱን ጣለ እርቃኑን ሰቀሉት በእንጨት ላይ ሃፍረቴን ሸፈነው እርሱ ሊታይ ዝቅ አለ ወረደ ያ ኤልሻዳይ አዝ፦ የመስቀሉ ፍቅር (4x) የመስቀሉ ፍቅር (4x) ለእኔ ነው መንክራተቱ መስቀል ላይ ውሎ መሞቱ ያኔ የፈሰሰው ደሙ አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ ስለእኔ ያለው ፍቅር ስለልጁ ነፍሱን እስከመስጠት ነበር እርሱ የእኔን በደል ጌታ ተሸከመ ተራራውን ወጣ ብዙ ደከመ ያኔ ቀራንዮ ሁሉ ተፈጸመ አዝ፦ የመስቀሉ ፍቅር (4x) የመስቀሉ ፍቅር (4x) ለእኔ ነው መንክራተቱ መስቀል ላይ ቅሎ መሞቱ ያኔ የፈሰሰው ደሙ አኑሮኛል ዛሬም በቤቱ