አዝ፦ አለ እንደገዛ አለ እንደከበረ (2x) ፍጥረት ሁሉ ያምልከው ይገባዋል እርሱ ጌታ ነው ኑ ደስ ይበለን በእርሱ ሃሴት እንዳድርግ በንጉሡ (2x) ኑ ደስ ኑ ደስ ይበለን ለእግዚአብሔር እንዘምር (4x) ለመድሃኒታችን ዕልል እንበል በምሥጋና ፊቱ ዘወትር እንቅረብ በዝማሬ እና በዕልልታ ሆታ ታላቅ እናድርገው ይህንን ጌታ ኑ ደስ ይበለን ለእግዚአብሔር እንዘምር (4x) የምድር ጥልቁቆች በእጁ ናቸው የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የእርሱ ናት እጁ የብስን አበጀ እጁ እኔን አበጀ የበላይነቱን ፍጥረት አወጀ (2x) አዝ፦ አለ እንደገዛ አለ እንደከበረ (2x) ፍጥረት ሁሉ ያምልከው ይገባዋል እርሱ ጌታ ነው ኑ ደስ ይበለን በእርሱ ሃሴት እንዳድርግ በንጉሡ ኑ ደስ ይበለን ለእግዚአብሔር እንዘምር (4x) የአህዛብ አማልክት ጣኦታት ናቸው ሁሉ ነገር ያላቸው ግን የሌላቸው የፍጥረት ሁሉ ጌታ ሰማይን ሰራ ክብር ይኸው በፊቱ ሞገስ ይኸው በፊቱ በመቅደሱ ውስጥ አለ ውበቱ (2x) አዝ፦ ኑ ደስ ኑ ደስ ይበለን ለእግዚአብሔር እንዘምር (4x) ለመድሃኒታችን ዕልል እንበል በምሥጋና ፊቱ ዘወትር እንቅረብ በዝማሬ እና በዕልልታ ሆታ ታላቅ እናድርገው ይህንን ጌታ ኑ ደስ ይበለን ለእግዚአብሔር እንዘምር (8x)