ዘመኔን የሰጠሁት ጉብዝናዬን ለእርሱ ያደረኩት አልጣለኝም አልረሳኝም ይዞ ሲመራኝ ሲያስመልጠኝ ሲያሻግረኝ ዛሬን አሳየኝ (2x) ስለዚህ ልበል ላውራው ልናገር የደረሰልኝ እርሱ እግዚአብሔር የተረሳውን አስታዋሽ እርሱ ዛሬም እላለሁ የለም እንደእርሱ ቀየረው ገብቶ በቤቴ አንገት መድፋት ቀረ በሕይወቴ ታማኝ ነው የምስኪን ወዳጅ ሁሉ አለ ስለሆንኩኝ ልጅ ሁሉ አለ ስለሆንኩኝ ልጅ ሁሉ አለ ስለሆንኩኝ ልጅ (2x) ገባ ገባ ገባ ኢየሱስ ቤቴ አማረ በእርሱ ሕይወቴ ተለወጠ ያ ማንነቴ አንድ ሰው ነኝ በመድሃኒቴ (2x) ቀናልኝ መንገዴ የሚያዋጣውን ይዤ ሁሉ አማረልኝ በዚህ በወዳጄ ክብርን ሳላስበው መጣ ወደቤቴ ተደላድያለሁ አርፌ በአባቴ ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ (2x) ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ ወዳጄ ቤቴ ሲገባ አባቴ ቤቴ ሲገባ ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ የጠራኝ ቤቴ ሲገባ ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ ምናገረው አለኝ ክተደረገልኝ ቸር ነው የእኔ አባት ዛሬ ላይ አቆመኝ አንደበቴን ልክፈት ላውራው ልመስክር ከጌታዬ ሌላ አልውቅም ክብር ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ (2x) ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ ወዳጄ ቤቴ ሲገባ አባቴ ቤቴ ሲገባ ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ የጠራኝ ቤቴ ሲገባ ኢየሱስ ቤቴ ሲገባ