Song Lyrics

በተዓምራትህ

Temesgen Markos
Yedem Kidan
በተዓምራትህ እየተገረምኩ በተዓምራትህ እየተደነቅኩ ዛሬም ላመልክህ/ላለነግስህ መቅደስህ ገባሁኝ (2x) አዝ፦ ይሄው የሽቶዬ መዓዛ ይሽተት ማደሪያህን ይሙላ ምክንያት አብዝቼ ላምልክ ፍቅርህ ወሰን የለው ልክ (5x) ሁልጊዜ ሁልጊዜ አዲስ ነህ አንተ ስትሰራ ተነግሮ ተነግሮ አያልቅም ሥራህ ቢወራ (2x) ቀና ብዬ ሳይህ ትሆናለህ ልዩ ተዓምር ስትሰራ ዓይኖቼ አንተን አዩ (2x) በአንደኛው (2x) ስገረም ሌላኛው ሲመጣ የአምላኬ የአድራጐቱ ብዛት ከውስጤ ሳይወጣ (2x) የአሰራሩ ሚስጥር ለእራሴ ሳይገባኝ በኃያልነቱ ጌታ እኔን መራኝ (2x) አዝ፦ ይሄው የሽቶዬ መዓዛ ይሽተት ማደሪያህን ይሙላ ምክንያት አብዝቼ ላምልክ ፍቅርህ ወሰን የለው ልክ (5x) ከፈተው ከፈተው አፌንም እንዳመሰግነው አስችሎኝ እንዲሁ እንዳልቀመጥ ምክንያቴን አበዛው (2x) ብዙ እያደረገ ዛሬ ላይ አቆመኝ በብቃቴ ሳይሆን በተዐምሩ አኖረኝ (2x) አዝ፦ ይሄው የሽቶዬ መዓዛ ይሽተት ማደሪያህን ይሙላ ምክንያት አብዝቼ ላምልክ ፍቅርህ ወሰን የለው ልክ (5x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection