ስሬት ያለበት ፈውስ አሮጌነትን ሽሮ የሚያደርግ አዲስ በደልን ሊያስወግድ ፈፅሞ ኃይል ያለው የጌታዬ ኢየሱስ ያ ክብሩ ደሙ ነው አዝ፦ ደሙ ኃይል ጉልበቴ ደሙ ሥር መሠረቴ ደሙ ሆነኝ ብቃቴ ደሙ መድኃኒቴ (2x) በደም የጠበቀ ቃልኪዳን ላይሻር ሊፋቅ ሊደመሰስ ከቶ እንዳይሞከር ስለገባው ጠላት በደም ተማምሎ ሊገድለኝ ሊያጠፋኝ ጥርሶቹን አሹሎ ወደ እኔ ሲመጣ በእራሱ ተማምሎ የእኔ ጌታ ኢየሱስ በእኔ ቦታ ሆኖ ያ የደምን ቃልኪዳን በደሙ አምክሮ ሕይወት ሆነልኝ ነውሬን ሸፍኖ አዝ፦ ደሙ ኃይል ጉልበቴ ደሙ ሥር መሠረቴ ደሙ ሆነኝ ብቃቴ ደሙ መድኃኒቴ (2x) በሰሩት ኃጢያት ልክ ማሰሪያ እንዲሆን ይሰዉ ነበረ የእንስሳቶችን ደም አቅም ያለውማ ይሰረይለታል መስዕዋት የሌለው እያነባ ይኖራል አለ ግን በሰማይ የድሃ አደግ አባት የሚራራ ሁሌ ለልጆቹ ሕይወት መቅረብ እንዲችሉ ፊቱ በእኩልነት ታሪክ ቀያየረ እርሱ ሆነ መስዕዋት አዝ፦ ደሙ ኃይል ጉልበቴ ደሙ ሥር መሠረቴ ደሙ ሆነኝ ብቃቴ ደሙ መድኃኒቴ (2x) አስጠንቅቆት ነበር የሞትን መልዓክ የእስራኤልን ሰፈር ከቶ እንዳይታወክ የተነገረውም እንደዚህ እኮ ነው ደንበር ላይ ካለ ትቶ እንዲያልፍ ነው አዎ በእኔ መንደር መታወክ አይሆንም አሳልፎ አይሰጠኝ የኢየሱሴ ደም ዛሬም ተማምኜ ኮራ ብዬ እሄዳለሁ በደም ነው የገዛኝ ዋጋዬ ውድ ነው አዝ፦ ደሙ ኃይል ጉልበቴ ደሙ ሥር መሠረቴ ደሙ ሆነኝ ብቃቴ ደሙ መድኃኒቴ (4x)