ለምንስ እፈራለሁ ኧረ ለምን እሰጋለሁ ታዲያ ለምን እፈራለሁ እኮ ለምን እሰጋለሁ አዝ፦ አምላኬ ከእኔ ጋራ ነው አይተወኝ እሱ ታማኝ ነው ሥጋቴ ኧረ ለምኔ ተዋጊው እያለ ጐኔ ዘለዓለሜን ይዞታል ከቶ አትፍራ ብሎኛል አሳርፎኝ በጉያው ስር ልምን ልፍራ እንዴት ልሸበር በእጁ መዳፍ ቀርጾኛል አበጃጅቶ ሰርቶኛል አንተ የእኔ ብሎኛል ሥጋት የለኝ አሳርፎኛል አዝ፦ አምላኬ/የጠራኝ ከእኔ ጋራ ነው አይተወኝ እሱ ታማኝ ነው ሥጋቴ ኧረ ለምኔ ተዋጊው እያለ ጐኔ (2x) የእኔ ነገር በእጁ ላይ ነው ሊያደርገው የታመነ ነው አላማዉም ከእንግዲህማ ቀን ቆጥሯል እሱ ሊመጣ በጊዜው ሁሉ ሆኖ ነገሬ በጌታ ሰምሮ አያለሁ ፍርሃቴ ይብቃ ቃል ወጥቷል ከቸሩ ጌታ ቃል እያለኝ ለምን እፈራለሁ የልጅነት ስልጣን የእኔ ነው ወጀቡንም በድል አዘዋለሁ አትፍራ ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋራ ነው በቃ ልረፍ ከእንግዲህ ሳልሰጋ የታምንኩት አለ ከእኔ ጋር ሁሉን ትቼ ሁሉን ለእርሱ ጥዬ ያለፍርሃል ልኑር . (1) . አዝ፦ የጠራኝ/አምላኬ ከእኔ ጋራ ነው አይተወኝ እሱ ታማኝ ነው ሥጋቴ ኧረ ለምኔ ተዋጊው እያለ ጐኔ (2x)