Song Lyrics

ክርስትና

Temesgen Markos
Yedem Kidan
አዝ፦ ዋጋ (3x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና ይታለፋል ይሁን ከጌታ ጋር የተዘጋጀልኝ ታላቅ ክብር መኖር ከኢየሱስ ጋር ክርስትና መጨረሻው ሲያምር ክርስትና (2x) መጨረሻው ሲያምር ታማኝ ሰው ሆኜለት ፈቃዱን ፈጽሜ ማለፍ እፈልጋለሁ በምድር እስካለሁ እኔ ዋጋ ቢያስከፍለኝ ጨክኜ አልፋለሁ ይረዳኛል ጌታ ያየልኝ ክብር ነው አዝ፦ ዋጋ (3x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና መቼ እንደዋዛ ይኖርና ክብር ዋጋ ያለው እርሱ የሞተለት አይደለም ሃይማኖት ክርስትና አለው ሽልማት ክርስትና (2x) አለው ሽልማት እሱን እያየሁኝ ሩጫውን እሮጣለሁ በእርግጥም አክሊሌን ከእጁ እረከባለሁ ውጣ ውረዱ ብዙ ቢሆንም መከራ ፍሬው ያማረ ነው እጅግ የሚያኮራ አዝ፦ ዋጋ (3x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና ይታለፋል ይሁን ከጌታ ጋር የተዘጋጀልኝ ታላቅ ክብር መኖር ከኢየሱስ ጋር ክርስትና መጨረሻው ሲያምር ክርስትና (2x) መጨረሻው ሲያምር ሃሳቡን ሃሳቤ አድርጌ ልቀበል በሞቴም የእርሱን ሞት ደግሞ እንድመስል ስጋን እስከ መሻቱ??? መስቀል ላይ ተሰቅዬ ልከተለው ወሰንኩ ያዋጣኛል ብዬ አዝ፦ ዋጋ (3x) ሚጠይቅ ነው ክርስትና መቼ እንደዋዛ ይኖርና ክብር ዋጋ ያለው እርሱ የሞተለት አይደለም ሃይማኖት ክርስትና አለው ሽልማት ክርስትና (2x) አለው ሽልማት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection