Song Lyrics

ተወለደ

Temesgen Markos
Sew Biteyek
የእግዚአብሔር ፈቃድ በልጁ ሊፈጸም ራሱን ዝቅ አድርጐ ወረደ ለዓለም በምድር ሊሰማ ሰላምና ደስታ ከድንግል ማሪያም ተወለደ ጌታ (4x) አዝ፦ ተወለደ (4x) ተወለደ (4x) እነሆ የምስራች እነሆ የምስራች ዛሬ በዳዊት ከተማ እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወለደ (4x) ተወለደ (4x) እረኞች ለማየት እጅጉን ጓጉለት ሰባ ሰገል መተው ወድቀው ሰገዱለት የፍጥረታት ጌታ የዓለም ሁሉ ንጉሥ ከአብ ሊያስታርቀን ተወለደ ኢየሱስ (4x) አዝ፦ ተወለደ (4x) ተወለደ (4x) መላዕክት አበሰሩ የምስራቹን ቃል ዛሬ በቤቴልሄም ወንድ ልጅ ተወልዷል ምድር ዕልል ትበል ታሰማ ምሥጋና ሕዝቡን የሚታደግ መሲህ መጥቷልና (4x) አዝ፦ ተወለደ (4x) ተወለደ (4x) እነሆ የምስራች እነሆ የምስራች ዛሬ በዳዊት ከተማ እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወለደ (4x) ተወለደ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection