Song Lyrics

ስለበላሁ

Temesgen Markos
Sew Biteyek
ስለበላሁ ስለጠጣሁ አልከተልህም እኔ ፈቃድህን እያደረኩ እኖራለሁ በዘመኔ (2x) አይረሳኝ ትላንት ያደረገው አስገረመኝ ለካ እርሱ ታማኝ ነው አሰናብቶ ሌላውን ሲሸኝ ሊሰራብኝ እኔን ግድ/ቆይ አለኝ (2x) አዝ፦ እኔስ የቀመስኩት እኔስ በዓይኔ ያየሁት ነገር አለ አንተ የሕይወት ቃል አለህ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ (2x) ጌታ አንተን ብዬ ስምህን ጠርቼ ነገር የሞላ ቀን ስራህን ሰርቼ በሆዴ እንዳልታለል ሲሞላ የልቡ ደርሶ እንዳይሸሽ ጥሎ እንዳይሄድ ባመጣው እግሩ ገስግሶ አይሆነው ያለአንተ ኑሮ ልቤ አውቆሃል ከአምናው ዘንድሮ አዝ፦ እኔስ የቀመስኩት እኔስ በዓይኔ ያየሁት ነገር አለ አንተ የሕይወት ቃል አለህ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ (2x) ወስኜ ተነሳሁ ልከተልህ አንተን ወደ ኋላ ትቼው የራሴን ነገሬን አንተው ጋር ይሻለኛል ቢሞላም ቢጐድልም ሁሉ ከደጅህ የትም አልሄድም እቤትህ ሁልጊዜ ሙሉ ደግ ነህ እጅህ ሰፊ ነው ዘመኔ ከእግሮችህ ስር ነው አዝ፦ እኔስ የቀመስኩት እኔስ በዓይኔ ያየሁት ነገር አለ አንተ የሕይወት ቃል አለህ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ ምርጫዬ ነህ መርጬሃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection