Song Lyrics

ተጽናና

Temesgen Markos
Sew Biteyek
መከራው በዝቶ ዛሬማ ጭንቅ ሆኖብሃል ሚያዝ ሚጨበጥ ከፊትህ ሁሉ ርቆሃል ተስፋ በመቁረጥ በርህን ዘግተህ ተቀምጠህ አበቃ የእኔማ ነገር ብልህ ደምድመህ ዜናው ዜናው ተሰማ የፍቅር አምላክ አለና ወገን ተጽናና አዝ፦ የመጽናናት አባት የርህራሄ አምላክ ከአንተ ጋር ነው ከአንቺ ጋር ነው ከእኛ ጋር ነው ከእኛ ጋር ነው (2x) ስለዚህ ወንድሜ ስለዚህ ወገኔ ተጽናና ኢየሱስ አለና (4x) ኢየሱስ አለና (4x) ተደግፈኸው አልጣለህ እርሱን ተማምነህ ተተግተኸው አልሸሸህ ደካማ ሆነህ ዓይኖቹ ዛሬም ያያሉ ከቶ አልደከሙም ሰፊ ትከሻው ብርቱ ነው ይሸከማሉ አይዞህ አይዞህ ተጽናና ክብርህን ጥለህ አምልከው ላደረገህ ቀና አዝ፦ የመጽናናት አባት የርህራሄ አምላክ ከአንተ ጋር ነው ከአንቺ ጋር ነው ከእኛ ጋር ነው ከእኛ ጋር ነው (2x) ስለዚህ ወንድሜ ስለዚህ ወገኔ ተጽናና ኢየሱስ አለና (4x) ኢየሱስ አለና (4x) ጌታ እያለ የምን ማዘን ነው ለእርሱ አስረክቦ እርፍ ማለት ነው ሃዘኔ ጠፍቶ እምባዬ ታብሷል ሁሉም አለፈ አስረስቶኛል አላዝንም ከእንግዲህ በቃ እኔ (4x) ጌታ እያለ ከጐኔ እርሱ እያለ ከጐኔ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection