Song Lyrics

ፊትህን ሳይ

Temesgen Markos
Sew Biteyek
ፊትህን ሳይ እጠግባለሁ ፊትህን ሳይ እጽናናለሁ እኔ እጽናናለሁ ፊትህን ሳይ እበረታለሁ ወደአንተ መጥቼ ሁሉነረሳለሁ እምባዬ ታብሶ ደስታን እሞላለሁ (2x) እራሴን ሳየው ማንነቴን ሳውቀው የደስታዬ ምንጭ ምንም የለም ከአንተ ውጭ አዝኜ መጥቼ ስቄ እመለሳለሁ ቀና ብዬ ሳይህ ፊትህ ጠጋ እላለሁ (2x) የመጽናኛዬ ቦታው የለቅሶ ሃዘኔ መርሻው ፊትህ ነው (3x) ደስ የሚያሰኘው ፊትህ ነው (3x) ደስ የሚያሰኘው (2x) ሌላ እኔ አልሻም የልብ የሚሆን የለም ሁሉም አላፊ የዚህ ዓለም ክብር ጠፊ ፊቴን መልሻለሁ አይጠቅመኝም ሌላ አንተኑን መመልከት ያዋጣኛልና (2x) የመጽናኛዬ ቦታው የለቅሶ ሃዘኔ መርሻው ፊትህ ነው (3x) ደስ የሚያሰኘው ፊትህ ነው (3x) ደስ የሚያሰኘው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection