ዛሬም ለቅሶ ዋይታ ዋይታ የዚህ ምድር ኑሮ የለውም እርካታ ጊዜው ሲደርስ ያኔ መምጫው የጌታዬ ፊት ለፊቴ ሳየው እርሱ ነው ደስታዬ (2x) አዝ፦ አላለቅስም አላለቅስም (2x) ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ (2x) ዘለዓለሜ በዚያ በክብር በአብ ቀኝ በደስታ ለመኖር በእርግጥ ናፍቄያለሁ ደርሳለሁ የታረደውን በግ መሲሁን አያለሁ (2x) አዝ፦ አላለቅስም አላለቅስም (2x) ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ በዚህ ምንም የለኝ የለኝ የሰው ዓይን ያላየው ያላየው በእጅ ያልተሰራው እርስቴ እንዴት ያማረ ነው የላይኛው ቤቴ (2x) አዝ፦ አላለቅስም አላለቅስም (2x) ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ የፍጥረት ሩጫ ሲገታ ለምድሩ በጊዜው ሲያበቃ ሙሽራው በድንገት ሲመጣ ፍጻሜን ያገኛል የቅዱሳን ተስፋ (2x) አዝ፦ አላለቅስም አላለቅስም (2x) ታይቶ ለሚጠፋ ከቶ አልቆርጥም ተስፋ የላይኛው ክብር ይበልጣል ከምድር ሃገሬ ሰማይ ነው ምን እፈልጋለሁ (2x)