Song Lyrics

ለየት አድርጐልኛል

የአምላኬ ስራው ይገርመኛል የኢየሱሴ ስራው ይደንቀኛል (2x) ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ሠማይን ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ምድርን አዝ፦ ይገርማል (3x) ሥራው ያስገርማል ይደንቃል (ይደንቃል) (3x) ሥራው ያስደንቃል ይሁን ብሎ ከፈጠራቸው በቃል ብቻ እርሱ ካደረጋቸው እኔን ለየት አድርጐኛል ጌታዬ በአምሳሉ ፈጥሮኛሉ (2x) ይሁን ብሎ ከፈጠራቸው በቃል ብቻ እርሱ ካዘዛቸው እኔን ለየት አድርጐኛል ጌታዬ በአምሳሉ ፈጥሮኛሉ (2x) ፍጥረትን ሲፈጥር የሚገርመኝ ለእኔ ሠማይ ይሁን አለ ሁነ ድሮ ያኔ ይሁን ከተባለው ለየት አድር እርሱን የምመስል ውብ አድርጐ ሰርቶኛል ገዢ አደረገኝ በፍጥረት ሁሉ ላይ የበላይ እንድሆን ትዛዝ ሰጠኝ ከላይ ልዩ ሰው አድርጐ በምድር አስቀመጠኝ ይሁን ብሎ ሳይሆን በእጆቹ ሰራኝ አዝ፦ ይገርማል (3x) ሥራው ያስገርማል ይደንቃል (ይደንቃል) (3x) ሥራው ያስደንቃል የአምላኬ ስራው እኔስ ይደንቀኛል ከአፉ የሚወጣው ቃል አስገርሞኛል ቃል ተናግሮ ብቻ ሁሉን ውብ አረገ እኔን በእራሱ አምሳል ቀርጾኝ ለየት አደረገ የአምላኬ ስራው ይገርመኛል የኢየሱሴ ስራው ይደንቀኛል (2x) ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ሠማይን ይሁን ይሁን ብሎ ፈጥሮ ምድርን አዝ፦ ይገርማል (3x) ሥራው ያስገርማል ይደንቃል (ይደንቃል) (3x) ሥራው ያስደንቃል ይሁን ብሎ ከፈጠራቸው በቃል ብቻ እርሱ ካዘዛቸው እኔን ለየት አድርጐኛል ጌታዬ በአምሳሉ ፈጥሮኛሉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection