አዝ፦ ነጋ ሌሊቱ ነጋ (4x) በሰላም አደርኩኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ እንደመሸ አልቀረም ሌሊቱ ነጋ ነጋ በሰላም አደርኩኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ አንበሶች አልበሉኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ንገሥ ! የታመንኩት ጌታ ያድነኛል ያልኩት የአንበሶችን አፍ ቆልፎ አየሁት (2x) ንጉሥ ሆይ ልንገርህ አምላኬ ጀግና ነው ተዓምርን ለማድረግ ለእርሱ ሁሉ ቀላል ነው ለጌታ ቀላል ነው [1] አዝ፦ ነጋ ሌሊቱ ነጋ (4x) በሰላም አደርኩኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ እንደመሸ አልቀረም ሌሊቱ ነጋ ነጋ በሰላም አደርኩኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ አንበሶች አልበሉኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ ንጉሥ ሆይ ልንገርህ ስማኝ ! ውስጤ ነገር አለ ጌታ ያስቀመጠዉ በአስጨነቀህ ጉዳይ መፍትሄ በእኔ አለ (2x) መቃብሬ ጉድጓድ በአንበሶች ማደሪያ በፍፁም አይሆንም አለው ብዙ ስራ (2x) [2] አዝ፦ ነጋ ሌሊቱ ነጋ (4x) በሰላም አደርኩኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ እንደመሸ አልቀረም ሌሊቱ ነጋ ነጋ በሰላም አደርኩኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ አንበሶች አልበሉኝ ሌሊቱ ነጋ ነጋ ንጉሥ ሆይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድምጠኝ ! ባለራዕይ ነኝ አልበላኝ አንበሳ ሰላም አድሪያለሁ በእርሱ የተነሳ ከጌታ የተነሳ አላሳፈረኝም የአመንኩት ጌታን ነው በላተኛው ትራስ ሆኖኝ አይቻለሁ (2x) [1] የዳንኤል አምላክ ነው ይህን ሁሉ የሰራው ሌቱ ነግቶልኛል ተራው የእኔ ነው የዳንኤል አምላክ ነው ይህን ያደረገው ሌቱ ነግቶልኛል ተራው የእኔ ነው ባለራዕይ ነኝ ተራው የእኔ ነው ውስጤ ነገር አለ ተራው የእኔ ነው በፍፁም አልሞትም ተራው የእኔ ነው ያወርሰኛል ገና ተራው የእኔ ነው ተራው የእኔ ነው (2x)