አዝ፦ የግሌ ነህ ወዳጄ (3x) የእራሴ ነህ ወዳጄ (3x) ወዳጅ የሚሏቸው አንድ ቀን ሲለዩ የቅርቤ ያልኳቸው ከአንተ ሰስተያዩ ግን አንተ ጥለህ የማትሄድ የማትከዳ አብዝተህ የምትወድ ወዳጄ ብዬ የማላፍርብህ አንተን ነው የእራሴ ያረኩህ (2x) የእራሴ አልኩኝ ጉያህ ሥር ሆኜ አንዳች ላይነካኝ በአንተ ታምኜ የግሌን ወዳጅ ማን ሊወስድብኝ ሌላውን ትቼ ስሩ ገባሁኝ የእራሴ አልኩኝ የእራሴ የእራሴ የእራሴ የግሌ የግሌ የግሌ አዝ፦ የግሌ ነህ ወዳጄ (3x) የእራሴ ነህ ወዳጄ (3x) ወዳጅ የሚሏቸው አንድ ቀን ሲለዩ የቅርቤ ያልኳቸው ከአንተ ሰስተያዩ ግን አንተ ጥለህ የማትሄድ የማትከዳ አብዝተህ የምትወድ ወዳጄ ብዬ የማላፍርብህ አንተን ነው የእራሴ ያረኩህ (2x) ከእንግዲህ አልፈራም ምን እሆን ብዬ የያዝኩት ታማኝ ሆኖኝ ጋሻዬ ጥሎኝ አልሄድም መንገድ ላይ ትቶ ና ልጄ እያለ እጄን ጐትቶ አስገባኝ ቀቶ አስገባኝ አስገባኝ አስገባኝ አስጠጋኝ አስጠጋኝ አስጠጋኝ ተደላደልኩኝ ወዳጅ አገኘሁ እፎይ የሚያስብል የሚመች ነው ጊዜ አይቶ አይርቅም ሁልጌዜ ያው ነው ስጋት አይገባኝ ልቤ ሙሉ ነው እፎይ ብያለሁ እፎዪ እፎዪ እፎዪ እፎይ (2x) አዝ፦ የግሌ ነህ ወዳጄ (3x) የእራሴ ነህ ወዳጄ (3x) ወዳጅ የሚሏቸው አንድ ቀን ሲለዩ የቅርቤ ያልኳቸው ከአንተ ሰስተያዩ ግን አንተ ጥለህ የማትሄድ የማትከዳ አብዝተህ የምትወድ ወዳጄ ብዬ የማላፍርብህ አንተን ነው የእራሴ ያረኩህ (2x)