በጨነቀኝ ጊዜ ፀሎቴ በእንባ ስነግርህ ጭንቀቴን ለካስ ሰምተኸኛል ተመሥገን ነዶ አስታቀፍከኝ ያማረውን አዝ፦ በዚያ በጣር ጊዜ ለሰማኸኝ በሄድኩበት ሁሉ ለመራኸኝ ይሰዋ በፊትህ ምሥጋናዬ ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (2x) ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (4x) ሁሉ አልፎ ዛሬ ዘምራለሁ የቃርሚያውን ሕይወት አልፌያለሁ እልፍ አደረገኝ አከበረኝ በአምላኬ ከፍታን አገኘሁኝ አዝ፦ በዚያ በጣር ጊዜ ለሰማኸኝ በሄድኩበት ሁሉ ለመራኸኝ ይሰዋ በፊትህ ምሥጋናዬ ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (2x) እንደመሸ አልቀረም ነግቶልኛል ከአምላኬ ጉብኝት ሆኖልኛል የጨለማው ዘመን አለፈና ልዘምር በቃሁኝ አልኩኝ ቀና አዝ፦ በዚያ በጣር ጊዜ ለሰማኸኝ በሄድኩበት ሁሉ ለመራኸኝ ይሰዋ በፊትህ ምሥጋናዬ ሰምሮልኝ አየሁኝ በአንተ ኑሮዬ (2x)