Song Lyrics

ተንስ አንተ ትውልድ

በውስጥህ እሳቴን አቀጣጥላለሁ የኃጢአትንም ዱር ጫካን እገልጣለሁ ነበልባሉ አይጠፋም ይነዳል ጨምሮ ሰሜኑን ይበላል ከደቡብ ጀምሮ ነውረኛውን ነገር ፈጽሞ እስኪያጠፋ የነበልባሉን ኃይል ማነው የሚያጠፋ ብቻ አንተ ተቀደስ ከነውር ተለይ ክብሬ በአንተ ላይ ነው ሊገለጥ ሊታይ አዝ፦ ተነስ አንተ ትውልድ ተነስ (2x) እቃ ጦርህን በአግባቡ ልበስ ያልታረሰውን ድንግሉን ለማረስ ጫማህን አጥልቅ ተነስ አንተ ተውልድ ተነስ ብዙ ስራ አለኝ በአንተ የምሰራው በመጀመሪያ ግን ቤቴን ነው ማጠራው እንዳትሆንብኝ ጥፋት ከሚያገኘው ዛሬ ቀን እያለ ተጠንቀቅ እልሃለሁ ይሄን ድምጼን ሰምተህ ቢቀናህ መንገድህ በምሰራበት ቀን ገንዘብ ትሆናለህ ሰባራውን ጠጋኝ አጋዥ ትባላለህ ድል ነሺ በመሆን ደግሞም ትከብራለህ አዝ፦ ተነስ አንተ ትውልድ ተነስ (2x) እቃ ጦርህን በአግባቡ ልበስ ያልታረሰውን ድንግሉን ለማረስ ጫማህን አጥልቅ ተነስ አንተ ተውልድ ተነስ የተጠራህበት ጥሪ ይህ ነውና ስራዬን ልትሰራ ጊዜው ቀርቧልና ቃሌን በደምብ ብላ በአግባቡ ጸልይ ሃሳቤ ይፈጸማል ያለው በሰማይ በምድር አምባሳደር ተወካዬ አንተ ነህ ስራዬን ለመስራት ከልብ ከተሰጠህ መጨረሻው ደርሷል የምገለጥበት ለሁሉም እንደስራው ዋጋ ምከፍልበት አዝ፦ ተነስ አንተ ትውልድ ተነስ (2x) እቃ ጦርህን በአግባቡ ልበስ ያልታረሰውን ድንግሉን ለማረስ ጫማህን አጥልቅ ተነስ አንተ ተውልድ ተነስ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection