Song Lyrics

ለእኔስ የደላኝ

አዝ፦ ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ በአንተ የታደለ የተመቸው እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው (2x) ለእኔስ የደላኝ የተመቸኝ እፎይ ያልኩበት ያሳረፈኝ እንደርሱ ማነው የሚደላ የሚመች የለም ከእርሱ ሌላ እርሱ ብቻ ነው የሆነኝ ከለላ አዝ፦ ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ በአንተ የታደለ የተመቸው እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው የምመካበት መመኪያዬ ምታመንበት መታመኚያዬ የምኮራበት ጽኑ ጋሻዬ ኢየሱሴ ነው ማረፊያዬ ታድያለሁ ሆኖኛል ጥላዬ አዝ፦ ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ በአንተ የታደለ የተመቸው እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው ጋሻ የሆነኝ ጽኑ መከታ ጉልበቴ እርሱ ነው እንዳልረታ በአንዳች አልሰጋም አልጨነቅም ሥጋቴን ወስዷል ሥጋት አላውቅም እፎይ ብያለሁ በመድሃኒያለም አዝ፦ ኢየሱስ በአንተ ሁሉ ሆኖ በዓይኔ አይቻለሁ ምስኪኑ ከብሮ በአንተ የታደለ የተመቸው እንደ እኔ ማነው ኧረ ማነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection