አበቃለት ብሎ ድንጋይ አትሞበት ዳግም እንዳይነሳ ሁሉን ዘጋግቶበት የእርሱ ነገር በቃ ከእንግዲህ በኋላ ትንሳኤ ዓይኖርም ምንም መፍትሄ መላ ደምድሞ ቁጭ ብሎ የበላይ ነኝ ሲል ድንገት ሳያስበው መጣበት ኃያል የሞት መውጊያን ሽሮ ጉድ ሰራው ጠላቴን ሕይወት ታወጀልን አንሞትም ሞት አንሞትም ሞትን አንሞትም ሞትን (2x) አዝ፦ ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ ኧረ ጉድ ጉድ ነው (2x) ጉድ አርጐ ተነሳ ሞትን አሸነፎ ኢየሱስ ተነሳ ያንን ክፉ ጉድ አደረገው ያንን ጨካኝ ጉድ አደረገው ሳትናኤልን ጉድ አደረገው ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ አደረገው ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ አደረገው የትንሳኤው ጌታ ሞትን አሸንፎ ኃይላትን አለቃን ሥልጣናትን ገፎ መቃብር አልያዘው ሁሉን ጥሶ ወጣ ለእኛም ተስፋን ሰጠን ደግሞ እንደሚመጣ ሰይጣንን ቀጥቅጦ ድልን ስላወጀ ለፍጥረት የእርቅ በር ድልድዩ ተበጀ በኢየሱስ ለአመንን አዲስ ኪዳን ሆነ አሮጌ አዳፋው ታሪክ ተከደነ ታሪክ ተከደነ ታሪክ ተከደነ (2x) አዝ፦ ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ ኧረ ጉድ ጉድ ነው (2x) ጉድ አርጐ ተነሳ ሞትን አሸነፎ ኢየሱስ ተነሳ ያንን ክፉ ጉድ አደረገው ያንን ጨካኝ ጉድ አደረገው ሳትናኤልን ጉድ አደረገው ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ አደረገው ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ አደረገው ያኔ በመስቀል ላይ ሁሉ ተፈጽሟል የእኔም ስራ ሁሉ በእዛ ሰዓት አልቋል የዜማ ጊዜ ነው ይሄ ዘመን ለእኔ ማመኔ እርግጥ ነው በኢየሱስ መዳኔ ሞቴን በሞት ሽሮ ሕይወትን ለሰጠኝ ዘምርለታለሁ በእርሱ ደስ እያለኝ ሳልሰጋ እኖራለሁ ከአምላኬ ጋራ ስማ ጠላቴ ሆይ ከቶ አንተን አልፈራ ከቶ አንተን አልፈራ ከቶ አንተን አልፈራ (2x) አዝ፦ ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ ኧረ ጉድ ጉድ ነው (2x) ጉድ አርጐ ተነሳ ሞትን አሸነፎ ኢየሱስ ተነሳ ያንን ክፉ ጉድ አደረገው ያንን ጨካኝ ጉድ አደረገው ሳትናኤልን ጉድ አደረገው ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ አደረገው ኧረ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ አደረገው