Song Lyrics

አንተ ባትረዳኝ ኖሮ

አዝ፦ የእኔ ጌታ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ወድቄ ነበረ ድሮ አባብዬ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ጠፍቼ ነበረ ድሮ (2x) ስወድቅ ምታነሳኝ እየደጋገፍከኝ አይዞህ እኔ አለሁ እያልክ ምታጽናናኝ በሃሩሩ ጊዜ ከለላ የሆንከኝ ዛሬን ደርሻለሁ ጥበቃህ በዝቶልኝ አዝ፦ የእኔ ጌታ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ወድቄ ነበረ ድሮ አባብዬ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ጠፍቼ ነበረ ድሮ ቀኜን ይዘህ አንተ ሁሌ እየመራኸኝ ከጐኔ ማትጠፋ ጋሻ እየሆንከኝ እንደ ዓይንህ ብሌን የተንከባከብከኝ ምከፍልህ የለኝም ምሥጋና ነው ያለኝ አዝ፦ የእኔ ጌታ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ወድቄ ነበረ ድሮ አባብዬ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ ጠፍቼ ነበረ ድሮ በዘመኔ ለአንተ አዜምልሃለሁ ከየት እንዳነሳኸኝ እኔ አውቀዋለሁ ጭራሽ አላየሁም እንደአንተ ያለ ጌታ በሰጠኸኝ ዘመን ላክብርህ ጠዋት ማታ አዝ፦ የእኔ ጌታ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ (የእኔ ጌታ) ወድቄ ነበረ ድሮ (ወድቄ ነበረ ድሮ) አባብዬ አንተ ባትረዳኝ ኖሮ (አባብዬ) ጠፍቼ ነበረ ድሮ (ጠፍቼ ነበረ ድሮ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection