Song Lyrics

በእውነት ለሚወዱህ

አዝ፦ በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (8x) መገፋት መሰደዴ ወደ ግብጽም መውረዴ ወዶኝ ነው ያደረገው አላማ በእኔ ስላለው ወጣሁ ቀኑ ደርሶ የበላይ አደረገኝ ተሾምኩኝ ተመረጥኩኝ ሁሉ ለበጐ ሆነልኝ (2x) ሁሉ ለበጐ ሆነልኝ (4x) አዝ፦ በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (4x) ሃዘን ሆነ መቸገሬ ኋላ ግን ሆነ ለክብሬ አለፍኩት እንደዋዛ መከራዬ ረግፎ እንደጤዛ ኑሮዬን እንዲህ አጣፍጦ ዘመርኩኝ ሁሉ ተረስቶ ሆነልኝ ሁሉ ለበጐ ጌታ ነገሬን ውብ አድርጐ (2x) ጌታ ነገሬን ውብ አድርጐ (4x) አዝ፦ በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (4x) አይበቃም እዘምራለሁ ለአምላኬ እኔ እቀኛለሁ አምሮልኝ ሁሉ ውብ ሆኗል መከራዬ ድልድይ ሆኖኛል ተሻገርኩ ሁሉን አልፌ አለሁኝ ከሞት ተርፌ አይቶልኝ እዚህ አድርሶኛል አክብሮ ያዘምረኛል (2x) አክብሮ ያዘምረኛል (4x) አዝ፦ በእውነት ለሚወዱህ እንደሃሳብህ ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ ነው ሁሉ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection