እወርሳለሁ (3x) ሃገሬን እወርሳለሁ አያለሁ (3x) አምላኬን አያለሁ አዝ፦ እኔስ እውርሳለሁ ሃገሬን ደርሼ አያለሁ አምላኬን በምኞት አልቀርም ደርሳለሁ አምላኬ ይረዳኛል አምናለሁ አየዋለሁ ጌታን አየዋለሁ አየዋለሁ እርሱን አየዋለሁ (2x) በጉዞ ላይ እያለሁ ብደናቀፍም ችግርም መከራ ቢፈራረቅም አንድ ቀን ይሄ ሁሉ ይቀርና እኔም እሰዋለሁ ለአምላኬ ምሥጋና አዜማለሁ ሁሌም አዜማለሁ አዜማለሁ ለጌታ አዜማለሁ (2x) አዝ፦ እኔስ እውርሳለሁ ሃገሬን ደርሼ አያለሁ አምላኬን በምኞት አልቀርም ደርሳለሁ አምላኬ ይረዳኛል አምናለሁ አየዋለሁ ጌታን አየዋለሁ አየዋለሁ እርሱን አየዋለሁ (2x) ተስፋ አስቆራጭ ነገር በአቋራጭ ቢነሳም እምነቴን ሊያስጥል በብርቱ ቢዋጋም ኢየሱስ ከጐኔ ነው ፍፁም ላይለየኝ ቃል ገብቶልኛል ጽዮንን ሊያወርሰኝ ሊያወርሰኝ ጌታ ሊያወርሰኝ ሊያወርሰኝ ኢየሱስ ሊያወርሰኝ (2x) አዝ፦ እኔስ እውርሳለሁ ሃገሬን ደርሼ አያለሁ አምላኬን በምኞት አልቀርም ደርሳለሁ አምላኬ ይረዳኛል አምናለሁ አየዋለሁ ጌታን አየዋለሁ አየዋለሁ እርሱን አየዋለሁ (2x) ጠላት ተስፋ ቁረጥ እኔ አምልጫለሁ ከዚህ ዓለም ሲቃ በኢየሱስ ድኛለሁ ጌታዬ ሲመጣ ሄዳለሁ አብሬ ዘለዓለም እኖራለሁ በሰማይ ሃገሬ በላይ ነው ቤቴ በላይ ነው ሰማይ ነው ሃገሬ ሰማይ ነው (3x)