Song Lyrics

አልቆምም

እጄን አልሰጥም ለሚጐትተኝ ፊት አልሳይም ለሚሟገተኝ የፊቴን እያየሁ እዘረጋለሁ መቆም አልሻም በእርሱ ፈጥናለሁ (2x) አዝ፦ አልቆምም (8x) ገና እሄዳለሁ በከፍታ ላይ እገሰግሳለሁ ኋላዬን ሳላይ አንዴ ቀብቶ ፈቶ ለቆኛል በእኔ የጀመረውን ገና ይቀጥላል (2x) አዝ፦ አልቆምም (8x) ጅምሩ ገና ታናሽ ቢሆንም ጥሶ ይሄዳል የሚይዘው የለም ቃልኪዳን አለኝ ከአምላኬ ጋር እርሱን አክብሬ እኔም ልከብር አዝ፦ አልቆምም (8x) ታምኜዋለሁ እንደሚረዳኝ እስከፍጻሜው እንደሚመራኝ እሄዳለሁኝ ክንዱን ታምኜ እወራሳለሁኝ የበላይ ሆኜ (2x) አዝ፦ አልቆምም (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection