Song Lyrics

ገና ነው ገና

ዞር በል አንተ ክፉ ሂድ ከአጠገቤ ተራዬን ልጨርስ ልድረስ እስከግቤ (2x) ጌታ ያየልኝንም ሄጄ እስክወርሰው መቆም አልፈልግም ልሂድ ላገልግለው (2x) አላለቀም ገና በእኔ የጀመረው አላለቀም ገና በእኔ የጀመረው ገለል በል ከፊቴ ጌታን ላገልግለው ጌታን ለጌልግለው (2x) በእኔ የጀመረውን ሳይፈጽም አይቀርም ታማኝ ነው በቃሉ ጌታ አይረሳኝም እንቅፋት ልትሆኑ ገና ከጅምሩ ቅባቱ እንዳይወጣ ይዛቹህ ልታስሩ አላማዬ ግቤ ኢየሱስ ነው ለእኔ አጠገቤ እትምጡ ዞርበሉ ከጐኔ አዝ፦ ገና ነው ገና ገና (2x) ቅባቱ በእኔ ላይ አላለቀምና ይጨምራል ገና ገና ነው ገና ገና (2x) ቅባቱ በእኔ ላይ አላለቀምና ይጨምራል ገና ይጨምራል ገና (4x) ገና እጓዛለሁ አምላኬን ታምኜ አብሬው ዞራለሁ ትከሻው ላይ ሆኜ ከእንግዲህ ላትደፍሩ ሂዱ ከዚህ በቃ አምላክ ከእኔ ጋር ነው የሁሉም አለቃ እርሱ ቀኜን እዟል ፈጽሞ ላይለቀኝ እከተለዋለሁ ጌታ ነው ሚያዋጣኝ አዝ፦ ገና ነው ገና ገና (2x) ቅባቱ በእኔ ላይ አላለቀምና ይጨምራል ገና ገና ነው ገና ገና (2x) ቅባቱ በእኔ ላይ አላለቀምና ይጨምራል ገና ይጨምራል ገና (4x) ብላቴና እያለሁ በትንሽነቴ ወንድሞቼን መርጦ ረስቶኝ ሳል አባቴ አምላኬ አስጠርቶኝ ቅባት ፈሶብኛል ለተለየ አላማው እኔን ፈልጐኛል ስሙን ማን ነው ያሉት ያ ያልተገረዘ የእስራኤልን ልብ እንዲህ የበዘበዘ ልሂድ ልጋጠመው በአምላኬ ሥም ልምታው በላዬ የፈሰሰው ሚዘርር ቅባት ነው አዝ፦ ገና ነው ገና ገና (2x) ቅባቱ በእኔ ላይ አላለቀምና ይጨምራል ገና ገና ነው ገና ገና (2x) ቅባቱ በእኔ ላይ አላለቀምና ይጨምራል ገና ይጨምራል ገና (፲2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection