ተኩላው ለምድ ለብሶ እውነትን አለባብሶ ሲዖል እንዳይከትህ ንቃ በል ወገኔ አስተውል አምልጥ ከጠላትህ ወዳጅ መስሎ ሳይገድልህ በጉብዝናህ ወራት አምላክህን አስብ ፈጣሪህን መዳን በሌላ የለም አትታለል ወገኔ እዳህን የከፈለው ይልሃል ና ወደኔ ከሞት መንገድ ተመለስ ኋላ ሳያጠፋህ ኢየሱስ ነው ከሲዖል ከሞት የሚያድንህ ሃብትህ ሞልቶ ቢትረፈረፍ ለዓለም ሁሉ ቢበቃ ዝናህ ከአጥናፍ አጥናፍ ቢደርስ ለጊዜውም ቢያስመካህ ስልጣን ዕውቀትም ቢኖርህ የነገሥታት ዘር ብትሆን ዋስትናህ ግን ኢየሱስ ነው ለነፍስህ ቤዛ የሚሆን አዝ፦ ቤዛህ ቤዛህ ቤዛህ ኢየሱስ ነው (4x) የሚደግፍህ የሌለ ብትሆንም ችግረኛ ተስፋ ቆርጠህ የምትባዝን ያለምንም መጽናኛ ለጥያቄዎችህ ሁሉ መልስ የሚሆን በእውነት ጌታ ኢየሱስ በደጅህ ነው በርህን ክፈትለት አስቀድመህ ከሁሉ አምላክህን ውደድ እንዲያሳይህ በጸጋው የሕይወትን መንገድ እሺ ብትል ለጌታ ብትታዘዝ ለቃሉ በበረከት ይሞላል የጐደለህ በሙሉ