Song Lyrics

ቃል ነው መሠረቴ

Tefera Negash
Alimelesim
አዝ፦ በጐርፍ በነፋስ አይወሰድም ቤቴ አስተማማኝ አለት ቃል ነው መሠረቴ (2x) ቃል ነው መሠረቴ ቃል ነው (4x) በእርሱ የታመነ ቤቱ አለት ላይ ነው ነፋሱም አይገፋው ወጀብ አይጥለው ሕያው የሚሰራ ቃል አለኝና አሻግሬ የማየው ድል አለ ገና አነስተኛ ቢመስልም ጅማሬዬ እጅግ ታላቅ ይሆናል ፍጻሜዬ ትምክህቴ ከላይ ነው ከአርያም ነገ ምን ይሆናል ብዬ አልሰጋም ሳልናወጥ መቆሜ ፍጥረት ሁሉ ደንቆታል የአምላኬ ሰላም ወርዶ ልቤን ሙሉ አድርጐታል አወዳደቁ ታላቅ መጨረሻው የከፋ እንደ አሸዋ ላይ ቤት አይደለም የኔ ተስፋ መኖሪያዬ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ለዘለዓለም (4x) ፀጋ ወርዶልኛል ከአርያም በፍፁም ወደኋላ አልልም ለሰማዩ ርስቴ እጋደላለሁ በአምላኬ ታምኜ እወርሰዋለሁ የሚያስጨንቀኝን በእርሱ ላይ ጥዬ በወደደኝ ጌታ ተደላልድዬ እተማመናለሁ በቃልኪዳኑ አይርድም ጉልበቴ ቢከፋም ቀኑ አዝ፦ በጐርፍ በነፋስ አይወሰድም ቤቴ አስተማማኝ አለት ቃል ነው መሠረቴ (2x) ቃል ነው መሠረቴ ቃል ነው (4x) ከመቅደሱ የወጣ የወረደ ከሰማይ እርሱ ነው መመኪያዬ የማዕዘኑ ድንጋይ በእምነት የታነጸ ጥብቅ ነው መሠረቴ በሽብር አይናጋ አይናወጥም ቤቴ መኖሪያዬ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ለዘለዓለም (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection