Song Lyrics

አልመለስም

Tefera Negash
Alimelesim
የከበረውን ከተዋረደው ለይቼ ዐይኔ ተገልጦልኝ አምላኬ ያየልኝን አይቼ ለሕያው ተስፋ ተለይቼያለሁ ወስኜ ንቄ ትቼዋለሁ ዓለማዊነትን ጨቅኜ በእውነት ተረትቻለሁ በእውነት ለሕይወት ተጠርቻለሁ ለሕይወት በፍቅር ተሸንፌአለሁ በፍቅር ለክብር ተለይቻለሁ ለክብር (እህም) መጐናጸፊያ ወድቆብኝ (እህ) እንድከተለው ጌታዬን (እህም) ሞፈር ቀንበሬን ሰብሬ (እህ) ጨክኜ ትቼው እርሻዬን (እህም) ምን ቀረኝ ብዬ ልመለስ (እህ) የያዝኩት ከእንቁ ይበልጣል (እህም) ሰው ክርስቶስ ተገልጦለት (እህ) ዓለምን እንዴት ይመርጣል አዝ፦ አልመለስም ወደኋላ አልመለስም (አልመለስም) (4x) በሆድ ሳልረሳ ከጥንቱ ያወቀኝ በእናቴ ማህጸን ሳለሁ የቀደሰኝ በአስደናቂ ፍቅሩ ልቤን አሸንፎ ተክሎኛል በቤቱ በምክሩ ደግፎ የዘለዓለሙን ተስፋ ጸንቶ የሚኖረውን በእጅ ያልተዳሰሰ የሰው ዐይን ያላየው ዋናዬን አግኝቻለሁ ከቶ አልመኝም ሌላ ዓለምና ምኞቱን አላይም ወደኋላ አዝ፦ አልመለስም ወደኋላ አልመለስም (አልመለስም) (4x) የከበረውን ከተዋረደው ለይቼ ዐይኔ ተገልጦልኝ አምላኬ ያየልኝን አይቼ ለሕያው ተስፋ ተለይቼያለሁ ወስኜ ንቄ ትቼዋለሁ ዓለማዊነትን ጨቅኜ በእውነት ተረትቻለሁ በእውነት ለሕይወት ተጠርቻለሁ ለሕይወት በፍቅር ተሸንፌአለሁ በፍቅር ለክብር ተለይቻለሁ ለክብር (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection